ኢያሱ 1:12-18

ኢያሱ 1:12-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ኢያ​ሱም ሮቤ​ል​ንና ጋድን የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል አስቡ፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ር​ፋ​ች​ኋል፤ ይህ​ች​ንም ምድር ይሰ​ጣ​ች​ኋል። ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሰ​ጣ​ችሁ በዚች ምድር ይቀ​መጡ፤ እና​ንተ፥ ጽኑ​ዓን ሁሉ ግን ታጥ​ቃ​ችሁ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ተዋ​ጉ​ላ​ቸው። አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በፀ​ሐይ መውጫ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ት​ማ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም ለኢ​ያሱ እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ለት፥ “ያዘ​ዝ​ኸ​ንን ነገር ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን ወደ​ም​ት​ል​ከ​ንም ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን። በሁ​ሉም ለሙሴ እንደ ታዘ​ዝን እን​ዲሁ ለአ​ንተ ደግሞ እን​ታ​ዘ​ዛ​ለን፤ ብቻ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን። ለአ​ንተ የማ​ይ​ታ​ዘዝ፥ የም​ታ​ዝ​ዘ​ው​ንም ቃል የማ​ይ​ሰማ ሁሉ፥ እርሱ ይገ​ደል፤ አሁ​ንም ጽና፥ በርታ።”

ኢያሱ 1:12-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢያሱ የሮቤልን ነገድ፣ የጋድን ነገድና የምናሴን ነገድ እኩሌታ እንዲህ አላቸው፤ “የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዲህ ሲል የሰጣችሁን ትእዛዝ አስቡ፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ ያሳርፋችኋል፤ ይህችንም ምድር ይሰጣችኋል።’ ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ እንዲሁም ከብቶቻችሁ ሙሴ በሰጣችሁ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ባለው ምድር ይቈዩ፤ ነገር ግን ተዋጊዎቻችሁ ሁሉ፣ ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ ከወንድሞቻችሁ ቀድመው ይሻገሩ፤ እናንተም ከወንድሞቻችሁ ጐን ተሰለፉ። ይህም፣ እግዚአብሔር እስኪያሳርፋቸውና ለእናንተም እንዳደረገው ሁሉ፣ እነርሱም እግዚአብሔር አምላካችሁ የሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚህ በኋላ እናንተም ተመልሳችሁ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የሰጣችሁን፣ በፀሓይ መውጫ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ምድር ትወርሳላችሁ።” እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ያዘዝኸንን ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ሁሉ እንሄዳለን። ለሙሴ ሙሉ በሙሉ እንደ ታዘዝን ሁሉ፣ ለአንተም እንታዘዛለን፤ ብቻ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋራ እንደ ነበረ፣ አሁንም ከአንተ ጋራ ይሁን። በትእዛዝህ ላይ የሚያምፅና ለቃልህ የማይታዘዝ ሁሉ ይገደል፤ ብቻ አንተ ጽና፤ አይዞህ፤ በርታ።”

ኢያሱ 1:12-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አያሱም የሮቤልን ልጆች የጋድንም ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛችሁን ቃል አስቡ፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር ያሳርፋችኋል፥ ይህችንም ምድር ይሰጣችኋል። ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጡ፥ ነገር ግን እናንተ፥ ጽኑዓን ኃያላን ሁሉ፥ ተሰልፋችሁ በወንድሞቻችሁ ፊት ተሻገሩ፥ እርዱአቸውም፥ እግዚአብሔር እናንተን እንዳሳረፋችሁ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፥ ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በፀሐይ መውጫ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትመለሳላችሁ ትወርሱአትማላችሁ። እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ እንሄዳለን። በሁሉም ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን፥ ብቻ አምላክህ እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን። በትእዛዝህ የሚያምፅ ሁሉ የምታዝዘውንም ቃል ሁሉ የማይሰማ፥ እርሱ ይገደል፥ ብቻ ጽና፥ አይዞህ።

ኢያሱ 1:12-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢያሱ የሮቤልንና የጋድን ነገዶች፥ እንዲሁም የምናሴን ነገድ እኩሌታ እንዲህ አላቸው፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህን ምድር ሰጥቶ ያሳርፋችኋል ብሎ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ቃል አስታውሱ። ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቈዩ፤ የጦር ልብስ ለብሰው ለውጊያ የተዘጋጁ ሰዎቻችሁ ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን ለመርዳት ግንባር ቀደም ሆነው ዮርዳኖስን ይሻገሩ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ለእናንተ እንደ ሰጠው ለወንድሞቻችሁም ዕረፍትን እስኪሰጥና እነርሱም እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ርስት እስኪያገኙ አብራችሁ ዝመቱ። ከዚያ በኋላ ተመልሳችሁ መጥታችሁ፥ በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ማዶ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሰጣችሁ በገዛ ምድራችሁ ትቀመጣላችሁ።” እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “የነገርከንን ሁሉ እንፈጽማለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን፤ ለሙሴ ሁልጊዜ ስንታዘዝለት እንደ ነበረ ሁሉ፥ ለአንተም እንታዘዛለን፤ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ፥ ከአንተም ጋር ይሁን! የአንተን ሥልጣን የሚቃወምና ትእዛዝህን ሁሉ የማይፈጽም ቢኖር በሞት ይቀጣ፤ ብቻ አንተ በርታ!”

ኢያሱ 1:12-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኢያሱም የሮቤልን ልጆች የጋድንም ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ “የጌታ ባርያ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛችሁን ቃል አስታውሱ፦ ‘ጌታ አምላካችሁ ያሳርፋችኋል፥ ይህችንም ምድር ይሰጣችኋል።’ ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጡ፤ ነገር ግን እናንተ፥ ጽኑዓን ኃያላን ሁሉ፥ ተሰልፋችሁ በወንድሞቻችሁ ፊት ተሻገሩ፥ እርዱአቸውም፥ ጌታ እናንተን እንዳሳረፋችሁ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፤ ከዚያም በኋላ የጌታ ባርያ ሙሴ በፀሐይ መውጫ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትመለሳላችሁ ትወርሱዋታላችሁም።” እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን። በሁሉም ነገር ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን፤ ብቻ ጌታ አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን። በትእዛዝህ የሚያምፅ ሁሉ የምታዝዘውንም ቃል ሁሉ የማይሰማ፥ እርሱ ይገደል፤ ብቻ ጽና፥ አይዞህ።”