ኢዩኤል 3:9-11 - Compare All Versions

ኢዩኤል 3:9-11 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“ይህን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ዐውጁ፤ ለሰ​ልፍ ተዘ​ጋጁ፤ ኀያ​ላ​ንን አስ​ነሡ፤ ሰል​ፈ​ኞች ሁሉ ይቅ​ረቡ፤ ይው​ጡም። ማረ​ሻ​ች​ሁን ሰይፍ፥ ማጭ​ዳ​ች​ሁ​ንም ጦር ለማ​ድ​ረግ ቀጥ​ቅጡ፤ ደካ​ማ​ውም፦ እኔ ብርቱ ነኝ ይበል። እና​ንተ በዙ​ሪያ ያላ​ችሁ አሕ​ዛብ ሁሉ፥ ፈጥ​ና​ችሁ ኑ፥ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ የዋ​ሃ​ንም ሰል​ፈ​ኞች ይሁኑ።

ኢዩኤል 3:9-11 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በሕዝቦች መካከል ይህን ዐውጁ፤ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ተዋጊዎችን አነሣሡ፤ ጦረኞችም ሁሉ ቀርበው ያጥቁ። ማረሻችሁ ሰይፍ፣ ማጭዳችሁም ጦር እንዲሆን ቀጥቅጡት፤ ደካማውም ሰው፣ “እኔ ብርቱ ነኝ” ይበል። እናንተ በዙሪያ ያላችሁ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ፈጥናችሁ ኑ፤ በዚያም ተሰብሰቡ።

ኢዩኤል 3:9-11 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፥ ለሰልፍ ተዘጋጁ፥ ኃያላንን አስነሡ፥ ሰልፈኞች ሁሉ ይቅረቡ ይውጡም። ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁንም ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፥ ደካማውም፦ እኔ ብርቱ ነኛ ይበል። እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ቸኵላችሁ ኑ፥ ተሰብሰቡ፥ አቤቱ፥ ኃያላኖችህን ወደዚያ አውርድ።

ኢዩኤል 3:9-11 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“ይህን ለአሕዛብ ሁሉ ዐውጁ፤ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ጀግኖችን ቀስቅሱ፤ ጦረኞቻችሁ ሁሉ ተሰብስበው ለጦርነት ይሰለፉ። ማረሻችሁ ሰይፍ፥ ማጭዳችሁም ጦር እንዲሆን ቀጥቅጡ፤ ደካማውም እንኳ ‘እኔ ብርቱ ነኝ’ ይበል፤ እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፤ በፍጥነት ውጡ! በሸለቆውም ተሰብሰቡ።”

ኢዩኤል 3:9-11 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፥ ለጦርነት ተዘጋጁ፥ ኃያላንን አስነሡ፥ ጦረኖች ሁሉ ይቅረቡ ይውጡም። ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁንም ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፥ ደካማውም፦ እኔ ብርቱ ነኛ ይበል። እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ቸኩላችሁ ኑ፥ ተሰብሰቡ፥ አቤቱ፥ ኃያላኖችህን ወደዚያ አውርድ።