ኢዮብ 41:1-11
ኢዮብ 41:1-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አትፈራምን? ለእኔ አዘጋጅተሃልና። የሚቃወመኝስ ማን ነው? የሚከራከረኝና በሕይወት የሚኖርስ ማን ነው? ከሰማይ በታች ያለውም ሁሉ የእኔ ነው። ስለ እርሱ ዝም አልልም፥ የኀይል ቃልም እንደ እርሱ ያለውን ይቅር ይለዋል። የፊቱን መጋረጃ ማን ይገልጣል? ወደ ደረቱ መጋጠሚያ ውስጥስ ማን ይገባል? የፊቱንስ ደጆች የሚከፍት ማን ነው? በጥርሶቹ ዙሪያም ግርማ አለ። አንጀቶቹ የናስ አራዊት ናቸው፤ የቆዳውም ጽናት እንደ ዓለት ድንጋይ ነው። እርስ በርሳቸው የተጣበቁ ናቸውና፥ ነፋስም በመካከላቸው መግባት አይችልም። ሰውን ከወንድሙ ጋር አንድ ያደርጋል፤ እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው፤ ሊለያዩም አይችሉም። እንጥሽታው ብልጭታን ያወጣል፥ ዐይኖቹም እንደ አጥቢያ ኮከብ ናቸው። ከአፉ የሚቃጠል መብራት ይወጣል የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል። የከሰል እሳት እንደሚቃጠልበት ምድጃ ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል።
ኢዮብ 41:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ሌዋታንን በመንጠቆ ልታወጣው፣ ወይም ምላሱን በገመድ ልታስረው ትችላለህን? መሰነጊያ በአፍንጫው ልታስገባ፣ ወይም ጕንጩን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህን? እርሱ እንድትምረው ይለማመጥሃል? በለስላሳ ቃላትስ ይናገርሃል? ለዘላለም ባሪያ ታደርገው ዘንድ፣ ከአንተ ጋራ ይዋዋላልን? እንደ ወፍ አልምደኸው ከርሱ ጋራ ልትጫወት ትችላለህ? ወይስ ለሴት አገልጋዮችህ መጫወቻነት ታስረዋለህን? ነጋዴዎችስ በርሱ ላይ ይከራከራሉን? ለቸርቻሪዎችስ ያከፋፍሉታል? ቈዳው ላይ ዐንካሴ ልትሰካ፣ ጭንቅላቱንም በዓሣ መውጊያ ጦር ልትበሳ ትችላለህን? እርሱን እስኪ ንካው፣ ግብግቡን ታስታውሳለህ፤ ከቶም አያላምድህም። እርሱን በቍጥጥር ሥር አውላለሁ ማለት ዘበት ነው፤ በዐይን ማየት እንኳ ብርክ ያስይዛል። ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፤ ማን ፊቱ ሊቆም ይችላል? ነክቶት በሰላም የሚሄድ ማን ነው? ከሰማይ በታች ማንም የለም።
ኢዮብ 41:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እነሆ፥ ተስፋው ከንቱ ነው፥ ያየው ሁሉ ስንኳ በፊቱ ይዋረዳል። ያንቀሳቅሰውም ዘንድ የሚደፍር የለም፥ እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማን ነው? እመልስለትስ ዘንድ መጀመሪያ የሰጠኝ ማን ነው? ከሰማይ ሁሉ በታች ያለው ገንዘቤ ነው። ስለ አካላቱና ስለ ብርቱ ኃይሉ፥ ስለ መልካም ሰውነቱ ዝም አልልም። የውጪ ልብሱን ማን ይገፋል? በጥንድ መንጋጋውስ ውስጥ ማን ይገባል? የፊቱንስ ደጆች የሚከፍት ማን ነው? በጥርሶቹ ዙሪያ ግርማ አለ። ቅርፊቶቹ ጠንካራ ስለ ሆኑ እርሱ ትዕቢተኛ ነው፥ በጠባብ ማተሚያ እንደ ታተሙ ናቸው። እርስ በርሳቸው የተቀራረቡ ናቸውና ነፋስ በመካከላቸው መግባት አይችልም። እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው፥ እስከማይለያዩም ድረስ ተያይዘዋል። እንጥሽታው ብልጭታ ያወጣል፥ ዓይኖቹም እንደ ወገግታ ናቸው። ከአፉ ፋናዎች ይወጣሉ፥ የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል።
ኢዮብ 41:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“ሌዋታን የሚባለውን የባሕር አውሬ በመንጠቆ ከባሕር ውስጥ ልትይዘው ትችላለህን? ወይም ምላሱን በገመድ ታስረዋለህን? በአፍንጫው መሰነጊያ አስገብተህ መንጋጋውንም በመንጠቆ ወግተህ ልትይዘው ትችላለህን? ምሕረት እንድታደርግለት ይለምንሃልን? በመልካም አነጋገር ይለምንሃልን? ለዘለዓለም በባርነት እንዲያገለግልህ ከአንተ ጋር ስምምነት ያደርጋልን? እንደ ወፍ እርሱን ልታለማምድ ትችላለህን? ወይስ ሴቶች ልጆችህን እንዲያጫውት አስረህ ታኖረዋለህን? ዓሣ ነጋዴዎች እርሱን ለመግዛት ይጫረታሉን? ቈራርጠውስ ይከፋፈሉታልን? ቆዳውን በፈለግህበት ቦታ በጦር መብሳት፥ ጭንቅላቱንም በሾተል ወግተህ መሰንጠቅ ትችላለህን? ከቻልክ እስቲ እጅህን በላዩ ላይ አሳርፍበት። ከእርሱ ጋር የምታደርገውን ትግል በፍጹም አትረሳውም፤ ዳግመኛም ከእርሱ ጋር ለመታገል አትሞክርም። “ከሌዋታን ጋር ታግሎ በቊጥጥር ሥር ለማዋል የሚደረግ ሙከራ ከንቱ ነው። እርሱን የሚያየው ሁሉ በፍርሃት ይብረከረካል። በእርሱ ላይ አደጋ መጣል ይህን ያኽል አደገኛ ከሆነ፥ ታዲያ፥ እኔን ለመቃወም የሚደፍር ማነው? ከሰማይ በታች ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ ታዲያ፥ እንድመልስለት ለእኔ ያበደረ ማነው?
ኢዮብ 41:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“እነሆ፥ ተስፋ ማድረግ ከንቱ ነው፥ እርሱን ማየቱ ብቻ ያብረከርካል። ማንም ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፥ እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማን ነው? እመልስለትስ ዘንድ መጀመሪያ የሰጠኝ ማን ነው? ከሰማይ ሁሉ በታች ያለው ገንዘቤ ነው። ስለ አካላቱና ስለ ብርቱ ኃይሉ፥ ስለ መልካም ሰውነቱም ዝም አልልም። የውጪ ልብሱን ማን ይገፋል? በጥንድ መንጋጋውስ ውስጥ ማን ይገባል? የፊቱንስ ደጆች የሚከፍት ማን ነው? በጥርሶቹ ዙሪያ ግርማ አለ። የጀርባው ቆዳዎች ጠንካራ ናቸው፤ አቤት ኩራት! በጥብቅ ማተሚያ እንደ ታተሙ ናቸው። እርስ በርሳቸው የተቀራረቡ ናቸውና ነፋስ በመካከላቸው መግባት አይችልም። እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው፥ እስከማይለያዩም ድረስ ተያይዘዋል። ሲያስነጥስ ብልጭታ ያወጣል፥ ዐይኖቹም እንደ ንጋት ወገግታ ናቸው። ከአፉ ፋናዎች ይወጣሉ፥ የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል።