ኢዮብ 4:4-6
ኢዮብ 4:4-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ቃሎችህ የሚሰናከሉትን ይደግፉ ነበር፤ የሚብረከረኩትንም ጒልበቶች ታበረታ ነበር። አሁን ግን ችግር ስለ መጣብህ ተስፋ ቢስ ሆነሃል፤ ችግሩም ስለ በረታብህ ተስፋ ቈርጠሃል። አምላክህን መፍራትህ መተማመኛህ፥ ትክክለኛ መንገዶችህም፥ ተስፋህ አይደለምን?
ያጋሩ
ኢዮብ 4 ያንብቡኢዮብ 4:4-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በቃልህ በሽተኞችን ታስነሣ ነበር፥ የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር። አሁን ግን ሕማም በአንተ ላይ መጥቶ ዳሰሰህ። አንተም ተቸገርህ። ጥንቱን ፍርሀትህ፥ ተስፋህም፥ የመንገድህም ጠማማነት፥ ስንፍና አይደለምን?
ያጋሩ
ኢዮብ 4 ያንብቡኢዮብ 4:4-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤ የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር። አሁን ግን መከራ አገኘህ፣ አንተም ተስፋ ቈረጥህ፤ ሸነቈጠህ፤ ደነገጥህም። ንጽሕናህ መታመኛህ፣ ቀና አካሄድህም ተስፋህ አይደለምን?
ያጋሩ
ኢዮብ 4 ያንብቡኢዮብ 4:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ቃልህ የሚሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጕልበት ታጸና ነበር። አሁን ግን በአንተ ላይ መጥቶአል፥ አንተም ደከምህ፥ ደርሶብሃል፥ አንተም ተቸገርህ። አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥ የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን?
ያጋሩ
ኢዮብ 4 ያንብቡ