ኢዮብ 39:1-2
ኢዮብ 39:1-2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“ዋልያ የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? የምታምጥበትንስ ጊዜ ትመለከታለህን? እርስዋ የምትወልድበትንስ ሙሉ ወራት ትቈጥራለህን? ከምጥስ ትገላግላታለህን?
ያጋሩ
ኢዮብ 39 ያንብቡኢዮብ 39:1-2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“የበረሓ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋሊያ ስታምጥስ ተከታትለህ አይተሃል? የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደ ሆነ ትቈጥራለህን? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህን?
ያጋሩ
ኢዮብ 39 ያንብቡኢዮብ 39:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የበረሃ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋላይቱስ የምታምጥበትን ጊዜ ትመለከታለህን? እርስዋ የምትፈጽመውንስ ወራት ትቈጥራለህን? የምትወልድበትንስ ጊዜ ታውቃለህን?
ያጋሩ
ኢዮብ 39 ያንብቡ