ኢዮብ 3:24-26
ኢዮብ 3:24-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከአዝመራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ስለ ደረሰብኝም አስፈሪ ነገር ሁልጊዜ አለቅሳለሁ። የተጠራጠርሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ ያሰብሁትም ደርሶብኛል። ተዘልዬ አልተቀመጥሁም፥ ፀጥታም አላገኘሁም፥ አላረፍሁም። ነገር ግን መከራ ደረሰችብኝ።”
ያጋሩ
ኢዮብ 3 ያንብቡኢዮብ 3:24-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ትካዜ ምግብ ሆኖኛልና፤ የሥቃይ ጩኸቴም እንደ ውሃ ይፈስሳል። የፈራሁት ነገር መጥቶብኛል፤ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል። ሰላም የለኝም፤ ርጋታም የለኝም፤ ሁከት እንጂ ዕረፍት የለኝም።”
ያጋሩ
ኢዮብ 3 ያንብቡኢዮብ 3:24-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከእንጀራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ጩኸቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል። የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል። ተዘልዬ አልተቀመጥሁም፥ አልተማመንሁም፥ አላረፍሁም፥ ነገር ግን መከራ መጣብኝ።
ያጋሩ
ኢዮብ 3 ያንብቡ