ኢዮብ 14:7-12
ኢዮብ 14:7-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ያቈጠቍጥ ዘንድ፥ ተስፋ አለው፤ ቅርንጫፉም አያልቅም። ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በጭንጫ ውስጥ ቢሞት፥ ከውኃ ሽታ የተነሣ ያቈጠቍጣል፤ እንደ አዲስ ተክልም ያፈራል። ሰው ግን ከሞተ ፈጽሞ ይተላል፤ ሟች ሰው ከሞተ በኋላ እንግዲህ አይኖርም። ባሕር ይጐድላል፤ ወንዙም ይነጥፋል፤ ይደርቅማል። ሰውም ከተኛ በኋላ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፤ ከእንቅልፉም አይነሣም።
ኢዮብ 14:7-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ዛፍ እንኳ ቢቈረጥ፣ እንደ ገና ሊያቈጠቍጥ፣ አዳዲስ ቅርንጫፍም ሊያበቅል ተስፋ አለው። ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅ፣ ጕቶው በመሬት ውስጥ ቢበሰብስም፣ የውሃ ሽታ ባገኘ ጊዜ ያቈጠቍጣል፤ እንደ ተተከለም ችግኝ ቅርንጫፍ ያወጣል። ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል? ውሃ ከባሕር ውስጥ እንደሚያልቅ፣ የወንዝ ውሃም ጠፍቶ እንደሚደርቅ፣ እንደዚሁም ሰው ይተኛል፤ ቀናም አይልም፤ ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቃም፤ ከእንቅልፉም አይነሣም።
ኢዮብ 14:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ያቈጠቍጥ ዘንድ፥ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው። ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥ ከውኃ ሽታ የተነሣ ያቈጠቍጣል፥ እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል። ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፥ ሰውም ነፍሱን ይሰጣል፥ እርሱስ ወዴት አለ? ውኃ ከባሕር ውስጥ ያልቃል፥ ወንዙም ያንሳል ይደርቅማል። ሰውም ተኝቶ አይነሣም፥ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥ ከእንቅልፉም አይነሣም።
ኢዮብ 14:7-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“ለተቈረጠ የዛፍ ጒቶ እንኳ ተስፋ አለው፤ እንደ ገና ሊያቈጠቊጥና ቅርንጫፎችም ሊያበቅል ይችላል። ምንም እንኳ ሥሮቹ በመሬት ውስጥ ቢያረጁ ግንዱም በዐፈር ውስጥ ቢበሰብስ፥ የውሃ ጠል ካገኘ እንደ ገና ያቈጠቊጣል፤ እንደ አዲስ ተክልም ቅርንጫፎችን ያወጣል። ሰው ግን ሞቶ እንዳልነበረ ይሆናል፤ ከሞተ በኋላስ የት ይገኛል? “የሐይቅ ውሃ ተኖ እንደሚያልቅ፥ የወንዝም ፈሳሽ እንደሚደርቅ፥ ሰውም እንዲሁ ከሞተ በኋላ አይመለስም፤ ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቃም፤ ከእንቅልፉም አይነሣም።
ኢዮብ 14:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“ዛፍ እንኳን ተሰፋ አለው፥ ቢቈረጥ የማቈጠቁጥ፥ ቅርንጫፉም የማደግ እድል አለው። ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥ በውኃ ሽታ ያቈጠቁጣል፥ እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል። ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፥ ሰውም ነፍሱ ትወጣለች፥ እርሱስ ወዴት አለ? ውኃ ከባሕር ውስጥ ያልቃል፥ ወንዙም ያንሳል ይደርቅማል። ሰውም እንዲሁ ተኝቶ አይነሣም፥ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥ ከእንቅልፉም አይነሣም።