ኢዮብ 13:5-12
ኢዮብ 13:5-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ላዳምጣችሁ አይገባኝም፥ ጥበብ ከእናንተ ጠፍታለችና። “አሁን የአፌን ክርክር ስሙ፥ የከንፈሬንም ፍርድ አድምጡ። በውኑ በእግዚአብሔር ፊት የምትናገሩ አይደላችሁምን? በፊቱ ሽንገላን ታወራላችሁን? ከእርሱ ወደ ኋላ ትመለሳላችሁን? እስኪ ራሳችሁ ፍረዱ። እርሱ ቢመረምራችሁ መልካም ነው፥ ይህን ሁሉ በኀይላችሁ ስታደርጉ ራሳችሁን ከእርሱ ጋር አንድ ታደርጋላችሁና። በስውር ለሰው ፊት ብታደሉ ዘለፋ ይዘልፋችኋል። ጥንቱን ኀይሉ አያስፈራችሁምን? ግርማስ ከእርሱ ዘንድ አይወድቅባችሁምን? ምሳሌያችሁ እንደ አመድ ዐላፊ ነው፤ ሥጋችሁም እንደ ትቢያ ነው።
ኢዮብ 13:5-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ምነው ዝም ብትሉ! ያ ከጥበብ ይቈጠርላችሁ ነበር። እንግዲህ ክርክሬን ስሙ፤ የከንፈሬንም አቤቱታ ስሙ። ለእግዚአብሔር ብላችሁ በክፋት ትናገራላችሁን? ስለ እርሱስ በማታለል ታወራላችሁን? ለርሱ ታደላላችሁን? ለእግዚአብሔር ጥብቅና ልትቆሙ ነውን? እርሱ ቢመረምራችሁ መልካም ነገር ይገኝባችኋልን? ሰውን እንደምታታልሉ፣ ልታታልሉት ትችላላችሁን? በስውር አድልዎ ብታደርጉ፣ በርግጥ እርሱ ይገሥጻችኋል። ግርማው አያስደነግጣችሁምን? ክብሩስ አያስፈራችሁምን? ምሳሌዎቻችሁ የዐመድ ምሳሌዎች ናቸው፣ መከላከያችሁም የጭቃ ምሽግ ነው።
ኢዮብ 13:5-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ! ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር። አሁንም ክርክሬን ስሙ፥ የከንፈሬንም ሙግት አድምጡ። በውኑ ስለ እግዚአብሔር ሐሰትን ትናገራላችሁን? ስለ እርሱም ሽንገላን ታወራላችሁን? ለፊቱስ ታደላላችሁን? ስለ እግዚአብሔርስ ትከራከራላችሁን? ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን? ወይስ በሰው እንደምትሳለቁ ትሳለቁበታላችሁን? በስውር ለሰው ፊት ብታደሉ ዘለፋ ይዘልፋችኋል። ክብሩስ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አይወድቅባችሁምን? ምስሌዎቻችሁ የአመድ ምሳሌዎች ናቸው፥ ምሽጎቻችሁ የጭቃ ምሽጎች ናቸው።
ኢዮብ 13:5-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ይልቅስ ዝም ብትሉ ኖሮ ጠቢባን መስላችሁ በታያችሁ ነበር! “የማቀርበውን ክርክር ስሙ፤ በደሌንም ስዘረዝር በጸጥታ አድምጡ። በእግዚአብሔር ስም ስለምን ሐሰት ትናገራላችሁ? በማታለል እግዚአብሔርን የምታስደስቱ ይመስላችኋልን? ለእርሱ ታደሉለታላችሁን? ለእርሱስ ጥብቅና ትቆማላችሁን? እግዚአብሔር ቢመረምራችሁ አንዳች መልካም ነገር ያገኝባችኋልን? ሰዎችን እንደምታሞኙ እግዚአብሔርንም ማሞኘት የምትችሉ ይመስላችኋልን? በስውር አድልዎ ብታደርጉ በእውነት እግዚአብሔር ይገሥጻችኋል። ክብሩ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አያስደነግጣችሁምን? ምሳሌያዊ አነጋገራችሁ እንደ ዐመድ ዋጋ ቢሶች ናቸው፤ ክርክራችሁም እንደ ሸክላ ተሰባብሮ ይወድቃል።
ኢዮብ 13:5-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ! ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር። አሁንም ክርክሬን ስሙ፥ የከንፈሬንም ሙግት አድምጡ። በውኑ ስለ እግዚአብሔር ሐሰትን ትናገራላችሁን? ስለ እርሱም ሽንገላን ታወራላችሁን? ለእርሱ እያዳላችሁ ነውን? ስለ እግዚአብሔርስ ትከራከራላችሁን? ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን? ወይስ በሰውን እንደምታታልሉ ልታታልሉት ትፈልጋላችሁን? በስውር ብታዳሉ በጥብቅ ይገሥጻችኋል። ክብሩስ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አይወድቅባችሁምን? ምስሌዎቻችሁ የአመድ ምሳሌዎች ናቸው፥ ምሽጎቻችሁ የጭቃ ምሽጎች ናቸው።”