ኢዮብ 11:13-18
ኢዮብ 11:13-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አንተ ልብህን ንጹሕ ብታደርግ፥ እጆችህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ በእጆችህ በደል ቢኖር ካንተ አርቀው፤ በልብህም ኀጢአት አይኑር፤ በዚያን ጊዜ ፊትህ በንጹሕ ውኃ እንደ ታጠበ ያበራል፥ መተዳደፍህንም ታስወግዳለህ፥ አትፈራምም። መከራህንም እንዳለፈ ማዕበል ትረሳለህ፥ ከእንግዲህም ወዲያ አትደነግጥም። ጸሎትህ እንደ አጥቢያ ኮከብ ይሆናል። ሕይወትህም እንደ ቀትር ብርሃን ያበራል። ተስፋህንም ታገኝ ዘንድ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፤ ያለ ኀዘንና ጭንቀትም በደኅንነት ትኖራለህ።
ኢዮብ 11:13-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣ በእጅህ ያለውን ኀጢአት ብታርቅ፣ ክፋትም በድንኳንህ እንዳይኖር ብታደርግ፣ በዚያ ጊዜ ሳታፍር ቀና ትላለህ፤ ያለ ፍርሀት ጸንተህ ትቆማለህ፤ መከራህን ትረሳለህ፤ ዐልፎ እንደ ሄደ ጐርፍም ታስበዋለህ። ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ያበራል፤ ጨለማውም እንደ ንጋት ይሆናል። ተስፋ ስላለ ተደላድለህ ትቀመጣለህ፤ ዙሪያህን ትመለከታለህ፣ ያለ ሥጋት ታርፋለህ።
ኢዮብ 11:13-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥ አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፥ ትበረታለህ፥ አትፈራምም። መከራህንም ትረሳለህ፥ እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ። ከቀትር ይልቅ ሕይወትህ ይበራል፥ ጨለማም ቢሆን እንደ ጥዋት ይሆናል። ተስፋም ስላለህ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፥ በዙሪያህ ትመለከታለህ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ።
ኢዮብ 11:13-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“ሆኖም፥ ልብህን የቀና ብታደርግ እጅህንም ዘርግተህ ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ፥ ኃጢአትን ከእጅህ ብታርቅ፥ ክፉ ነገርም በቤትህ እንዲገኝ ባታደርግ፥ በዚያን ጊዜ ቀና ብለህ ያለ ኀፍረት ሁሉን ነገር ታያለህ፤ ያለ ፍርሀትም ጸንተህ መቆም ትችላለህ። ችግርህን ሁሉ ትረሳዋለህ፤ የምታስታውሰውም እንዳለፈ ጐርፍ ብቻ ነው። ሕይወትህ ከቀትር ፀሐይ ይበልጥ ይበራል፤ ጨለማው እንደ ማለዳ ብርሃን ይሆናል። ተስፋ ስላለህ አንተም በመተማመን ትኖራለህ፤ እግዚአብሔር ስለሚጠብቅህ ያለ ስጋት ዐርፈህ ትኖራለህ።
ኢዮብ 11:13-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጆችህን ወደ እርሱ ትዘረጋለህ፥ በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥ በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፥ ትበረታለህ፥ አትፈራምም። መከራህንም ትረሳለህ፥ እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ። ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ያበራል፥ ጨለማም ቢሆን እንደ ጥዋት ይሆናል። ተስፋም ስላለህ ተማምነህ ትቀመጣለህ፥ በዙሪያህ ትመለከታለህ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ።