ዮሐንስ 6:66-69
ዮሐንስ 6:66-69 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ስለዚህም ከደቀ መዛሙርቱ ወደ ኋላቸው የተመለሱ ብዙዎች ናቸው፤ ከዚያም ወዲህ አብረውት አልሄዱም። ጌታችን ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን፥ “እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትሻላችሁን?” አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘለዓለም የሕይወት ቃል እያለህ ወደ ማን እንሄዳለን? እኛስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ እንደ ሆንህ አምነናል፤ አውቀናልም።”
ዮሐንስ 6:66-69 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚህም በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ከዚያም ወዲያ አልተከተሉትም። ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን፣ “እናንተም ደግሞ መሄድ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ጌታ ሆይ፤ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ አንተ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደ ሆንህ አምነናል፤ ዐውቀናልም።”
ዮሐንስ 6:66-69 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም። ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ፦ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ። ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።
ዮሐንስ 6:66-69 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በዚህም ምክንያት ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ኢየሱስን መከተል ተዉ። ስለዚህ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት፥ “እናንተም ደግሞ መሄድ ትፈልጋላችሁን?” አላቸው። በዚህ ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃል አለህ። እኛስ አምነናል፤ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ አንተ እንደ ሆንክም ዐውቀናል።”