ዮሐንስ 6:35-45

ዮሐንስ 6:35-45 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚ​መጣ ከቶ አይ​ራ​ብም፤ በእኔ የሚ​ያ​ም​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም። ነገር ግን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አያ​ች​ሁኝ፤ አላ​መ​ና​ች​ሁ​ብ​ኝ​ምም። አብ የሚ​ሰ​ጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመ​ጣል፤ ወደ እኔ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ከቶ ወደ ውጭ አላ​ወ​ጣ​ውም። ከሰ​ማይ የወ​ረ​ድሁ የላ​ከ​ኝን ፈቃድ እንጂ፥ ፈቃ​ዴን ላደ​ርግ አይ​ደ​ለ​ምና። የላ​ከኝ የአብ ፈቃ​ድም ይህ ነው፤ ከሰ​ጠኝ ሁሉ አን​ድስ እንኳ ቢሆን እን​ዳ​ይ​ጠፋ ነው፤ ነገር ግን እኔ በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ። የአ​ባቴ ፈቃዱ ይህ ነው፤ ወል​ድን አይቶ የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ ነው፤ እኔም በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ።” አይ​ሁ​ድም ስለ እርሱ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤ “ከሰ​ማይ የወ​ረደ የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ” ብሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና። “እኛ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን የም​ና​ው​ቃ​ቸው ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ ኢየ​ሱስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወረ​ድሁ ይለ​ናል?” አሉ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርስ በር​ሳ​ችሁ አታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ። የላ​ከኝ አብ ካል​ሳ​በው በቀር ወደ እኔ መም​ጣ​ትን የሚ​ችል የለም፤ እኔም በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን አስ​ነ​ሣ​ዋ​ለሁ። ‘ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ማሩ ይሆ​ናሉ’ ተብሎ በነ​ቢ​ያት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል፤ እን​ግ​ዲህ ከአ​ባቴ የሰማ ሁሉ ተምሮ ወደ እኔ ይመ​ጣል።

ዮሐንስ 6:35-45 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔም የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም። ነገር ግን እንደ ነገርኋችሁ፣ አይታችሁኝም እንኳ አታምኑም። አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤ ከሰማይ የወረድሁት የራሴን ፈቃድ ለማድረግ ሳይሆን፣ የላከኝን የርሱን ፈቃድ ለመፈጸም ነውና፤ የላከኝም ፈቃድ፣ ከሰጠኝ ሁሉ አንድ እንኳ ሳይጠፋብኝ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣ ነው። የአባቴ ፈቃድ ወልድን አይቶ በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” አይሁድም፣ “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ” በማለቱ ያጕረመርሙበት ጀመር። ደግሞም፣ “ይህ አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው፣ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? ታዲያ አሁን እንዴት፣ ‘ከሰማይ ወረድሁ ይላል’  ” አሉ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እርስ በርሳችሁ አታጕረምርሙ፤ የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ማንም ወደ እኔ መምጣት አይችልም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። በነቢያትም፣ ‘ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ’ ተብሎ ተጽፏል፤ አብን የሚሰማና ከርሱም የሚማር ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።

ዮሐንስ 6:35-45 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፥ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም። ነገር ግን አይታችሁኝ እንዳላመናችሁ አልኋችሁ። አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤ ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና። ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳልጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው። ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። እንግዲህ አይሁድ፦ ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ ስላለ ስለ እርሱ አንጐራጐሩና፦ አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ፦ ከሰማይ ወርጃለሁ እንዴት ይላል? አሉ። እርስ በርሳችሁ አታንጐራጕሩ። የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሁሉም ከእግዚአብሔ የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።

ዮሐንስ 6:35-45 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ፈጽሞ አይራብም፤ በእኔ የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም፤ እናንተ ግን አይታችሁኛል፤ ግን በእኔ አላመናችሁም እላችኋለሁ። አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ፈጽሞ ወደ ውጪ አላባርረውም። እኔ ከሰማይ የወረድኩት የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ እንጂ የራሴን ፈቃድ ለማድረግ አይደለም። የላከኝ ፈቃድ፥ ከሰጠኝ ሁሉ አንድ እንኳ ሳላጠፋ በመጨረሻው ቀን ከሞት እንዳስነሣቸው ነው። አዎ! የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያይና በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።” ስለዚህ ኢየሱስ “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ” በማለቱ አይሁድ በእርሱ ላይ አጒረመረሙ፤ እንዲህም አሉ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? አባቱንና እናቱንስ እናውቃቸው የለምን? ታዲያ፥ አሁን እርሱ እንዴት ‘ከሰማይ ወረድኩ’ ይላል?” ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እርስ በርሳችሁ አታጒረምርሙ፤ የላከኝ አብ የሳበው ካልሆነ በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚችል ማንም የለም፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም በመጨረሻ ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ። በነቢያት መጻሕፍት ‘ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ’ ተብሎ ተጽፎአል፤ ስለዚህ ከአብ ሰምቶ የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።

ዮሐንስ 6:35-45 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም በፍጹም አይጠማም። ነገር ግን እንዳያችሁኝ፥ እንዳላመናችሁም ነገርኳችሁ። አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላስወጣውም፤ ፈቃዴን ለማድረግ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና። የላከኝ የአብ ፈቃድም ይህ ነው፤ ከሰጠኝ ሁሉ አንድም እንኳን እንዳላጠፋ፥ ይልቁንም በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው ነው። የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፤ ወልድን አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” አይሁድም “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ፤” በማለቱ ማንጐራጐር ጀመሩ፤ “ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? አባቱንና እናቱን እናውቃቸው የለምን? ታዲያ ‘ከሰማይ ወርጃለሁ’ እንዴት ይላል?” አሉ። ኢየሱስም መለሰ፥ አላቸውም፦ “እርስ በእርሳችሁ አታንጐራጉሩ። የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚችል የለም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ‘ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤’ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማና የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።

ዮሐንስ 6:35-45

ዮሐንስ 6:35-45 NASVዮሐንስ 6:35-45 NASVዮሐንስ 6:35-45 NASVዮሐንስ 6:35-45 NASV