ዮሐንስ 20:19-29

ዮሐንስ 20:19-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ያም ከሳ​ም​ንቱ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቤት ደጁ ተቈ​ልፎ ሳለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው። ይህ​ንም ብሎ እጆ​ቹ​ንና ጎኑን አሳ​ያ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጌታ​ች​ንን ባዩት ጊዜ ደስ አላ​ቸው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዳግ​መኛ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ አብ እኔን እንደ ላከኝ እን​ዲሁ እኔ እና​ን​ተን እል​ካ​ች​ኋ​ለሁ።” ይህ​ንም ብሎ እፍ አለ​ባ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​በሉ። ኀጢ​ኣ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ያላ​ች​ሁ​ላ​ቸው ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይቅር ያላ​ላ​ች​ኋ​ቸው ግን አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ውም።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመጣ ጊዜ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ከዐ​ሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት አንዱ ቶማስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር አል​ነ​በ​ረም። ሌሎች ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም፥ “ጌታ​ች​ንን አየ​ነው” አሉት፤ እርሱ ግን፥ “የች​ን​ካ​ሩን ምል​ክት በእጁ ካላ​የሁ፥ ጣቴ​ንም ወደ ተቸ​ነ​ከ​ረ​በት ካል​ጨ​መ​ርሁ፥ እጄ​ንም ወደ ጎኑ ካላ​ገ​ባሁ አላ​ም​ንም” አላ​ቸው። ከስ​ም​ንት ቀን በኋ​ላም ዳግ​መኛ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ በው​ስጡ ሳሉ፥ ቶማ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው ሳለ በሩ እንደ ተዘጋ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው። ከዚ​ህም በኋላ ቶማ​ስን፥ “ጣት​ህን ወዲህ አም​ጣና እጆ​ችን እይ፤ እጅ​ህ​ንም አም​ጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠ​ራ​ጣሪ አት​ሁን” አለው። ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ አም​ላ​ኬም” ብሎ መለሰ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ስለ አየ​ኸኝ አመ​ን​ህን? ብፁ​ዓ​ንስ ሳያዩ የሚ​ያ​ምኑ ናቸው” አለው።

ዮሐንስ 20:19-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚያ ዕለት፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በምሽት፣ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን በመፍራት በሮቹን ቈልፈው ተሰብስበው ሳለ፣ ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። ይህንም ብሎ እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው፤ ደቀ መዛሙርትም ጌታን ባዩት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው። ኢየሱስም እንደ ገና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን! አብ እኔን እንደ ላከኝ፣ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው። ይህን ካለ በኋላም፣ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ብትሉ፣ ኀጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል፤ ኀጢአታቸውን ይቅር ባትሉ ግን፣ ይቅር አይባልላቸውም።” በዚህ ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው፣ ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ፣ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ አልነበረም። ሌሎች ደቀ መዛሙርትም፣ “ጌታን አየነው እኮ!” አሉት። እርሱ ግን፣ “በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየሁ፣ ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ጣቴን ካላደረግሁ፣ በጐኑም እጄን ካላስገባሁ አላምንም” አለ። ከስምንት ቀን በኋላም፣ ደቀ መዛሙርቱ በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋራ ነበር፤ በሮቹ ተቈልፈው ነበር፤ ኢየሱስ ግን መጥቶ በመካከላቸው ቆመና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። ከዚያም ቶማስን፣ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ፤ እጆቼንም ተመልከት፤ እጅህን ዘርጋና በጐኔ አስገባ፤ አትጠራጠር፤ እመን” አለው። ቶማስም፣ “ጌታዬ፤ አምላኬም!” አለው። ኢየሱስም፣ “አንተ ስላየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብፁዓን ናቸው” አለው።

ዮሐንስ 20:19-29 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ይህንም ብሎ እጆቹንም ጎኑንም አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው። ኢየሱስም ዳግመኛ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ” አላቸው። ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፦ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” አላቸው። ነገር ግን ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከእነርሱ ጋር አልነበረም። ሌሎቹም ደቀ መዛሙርቱ፦ “ጌታን አይተነዋል” አሉት። እርሱ ግን፦ “የችንካሩን ምልክት በእዶቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም” አላቸው። ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ “ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን” አለው። ቶማስም፦ “ጌታዬ አምላኬም” ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም፦ “ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው ናቸው” አለው።

ዮሐንስ 20:19-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በዚያው በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን እሑድ ማታ ደቀ መዛሙርቱ የአይሁድን ባለሥልጣኖች በመፍራት፥ በራፎቹን ዘግተው፥ በቤት ውስጥ ተሰብስበው ነበር፤ በሮቹ ተዘግተው ሳለ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ተሰበሰቡበት ቤት ገባ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። ይህንንም ብሎ እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንደገና “ሰላም ለእናንተ ይሁን! አብ እኔን እንደ ላከኝ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው። ይህን ብሎ እፍ አለባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤ እናንተ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ብትሉ ይቅር ይባልላቸዋል፤ እናንተ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ባትሉ ግን፥ ይቅር አይባልላቸውም” አላቸው። ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ በመጣ ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ፥ ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም። ስለዚህ ሌሎች ደቀ መዛሙርት ቶማስን “ጌታን አየነው” አሉት። እርሱ ግን “በምስማር የተወጉትን እጆቹን ካላየሁና ጣቴን በምስማር በተወጋው ውስጥ ካላገባሁ፥ እጄንም በጐኑ ቊስል ካላገባሁ አላምንም” አላቸው። ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ እንደገና በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም አብሮአቸው ነበር፤ በሮቹ ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። ከዚህ በኋላ ቶማስን፥ “ጣትህን ወዲህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጐኔ ውስጥ አግባው፤ እመን እንጂ እምነተ ቢስ አትሁን” አለው። ቶማስም “ጌታዬ! አምላኬም!” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም ቶማስን፥ “አንተስ ስለ አየኸኝ አመንክ፤ ሳያዩኝ የሚያምኑ ግን የተመሰገኑ ናቸው” አለው።

ዮሐንስ 20:19-29 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በዚያው ከሳምንቱ የመጀመሪያው በሆነው ቀን፥ በመሸ ጊዜ፥ ደቀመዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ይህንንም ብሎ እጆቹንም ጎኑንም አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው። ኢየሱስም ዳግመኛ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ፤” አላቸው። ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። ኀጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል፤” አላቸው። ነገር ግን ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከእነርሱ ጋር አልነበረም። ሌሎቹም ደቀመዛሙርቱ “ጌታን አይተነዋል፤” አሉት። እርሱ ግን “የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ላይ ካላየሁ፥ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ውስጥ ካላስገባሁ፥ እጄንም በጎኑ ቊስል ውስጥ ካላስገባሁ አላምንም፤” አላቸው። ከስምንት ቀን በኋላም ደቀመዛሙርቱ ደግመው በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ከዚያም በኋላ ቶማስን “ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ ውስጥ አስገባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን፤” አለው። ቶማስም “ጌታዬና አምላኬ!” ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም “ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው” አለው።