ዮሐንስ 19:16-18
ዮሐንስ 19:16-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዚህ በኋላ ሊሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ጌታችን ኢየሱስንም ተቀብለው ወሰዱት። መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፤ ከእርሱም ጋር አንዱን በቀኝ፥ አንዱንም በግራ አድርገው ሌሎች ሁለት ወንበዴዎችን ሰቀሉ፤ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ።
ያጋሩ
ዮሐንስ 19 ያንብቡዮሐንስ 19:16-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በመጨረሻም ጲላጦስ እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው። ወታደሮቹም ኢየሱስን ይዘው ወሰዱት፤ እርሱም የራሱን መስቀል ተሸክሞ በአራማይክ “ጎልጎታ” ተብሎ ወደሚጠራው “የራስ ቅል” ወደተባለው ቦታ ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፤ ከርሱም ጋራ ሁለት ሰዎች፣ አንዱን በዚህ በኩል፣ ሌላውን በዚያ በኩል፣ ኢየሱስንም በመካከል አድርገው ሰቀሉ።
ያጋሩ
ዮሐንስ 19 ያንብቡዮሐንስ 19:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ስለዚህ በዚህን ጊዜ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው። ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ።
ያጋሩ
ዮሐንስ 19 ያንብቡ