ዮሐንስ 15:1-8

ዮሐንስ 15:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“እው​ነ​ተኛ የወ​ይን ሐረግ እኔ ነኝ፤ ተካ​ዩም አባቴ ነው። በእኔ ያለ​ውን፥ ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫ​ፍም ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ደ​ዋል፤ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እን​ዲ​ያ​ፈራ ያጠ​ራ​ዋል። እና​ንተ ግን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ቃል ፈጽ​ማ​ችሁ ንጹ​ሓን ናችሁ። በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእ​ና​ንተ፤ ቅር​ን​ጫፍ በወ​ይኑ ግንድ ከአ​ል​ኖረ ብቻ​ውን ሊያ​ፈራ እን​ደ​ማ​ይ​ችል እና​ን​ተም እን​ዲሁ በእኔ ካል​ኖ​ራ​ችሁ ፍሬ ማፍ​ራት አት​ች​ሉም። እኔ የወ​ይን ግንድ ነኝ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም እና​ንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚ​ኖር እኔም በእ​ርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚ​ያ​ፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድ​ረግ አት​ች​ሉ​ምና። በእኔ የማ​ይ​ኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅር​ን​ጫፍ ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ ሰብ​ስ​በ​ውም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል። በእ​ኔም ብት​ኖሩ ቃሌም በእ​ና​ንተ ቢኖር የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ሁ​ማል። ብዙ ፍሬ ብታ​ፈሩ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቴም ብት​ሆኑ በዚህ አባቴ ይከ​በ​ራል።

ዮሐንስ 15:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“እውነተኛው የወይን ተክል እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው። እርሱም በእኔ ያለውን፣ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን የበለጠ እንዲያፈራ ይገርዘዋል። ከነገርኋችሁ ቃል የተነሣ እናንተ አሁን ንጹሓን ናችሁ። በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ካልሆነ በቀር ብቻውን ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፤ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም። “እኔ የወይን ተክል ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ማንም በእኔ ቢኖር እኔም በርሱ ብኖር፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና። በእኔ የማይኖር ተጥሎ እንደሚደርቅ ቅርንጫፍ ነው፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተለቅመው ወደ እሳት ይጣላሉ፤ ይቃጠላሉም። በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም። ብዙ ፍሬ በማፍራት ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብትገልጡ፣ በዚህ አባቴ ይከብራል።

ዮሐንስ 15:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው፤ በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል። እናንተም ስለ ነገርኳችሁ ቃል አሁን ንጹሖች ናችሁ። በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ጸንቶ ካልኖረ በቀር በራሱ ብቻ ፍሬ ማፍራት እንደማይቻለው እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም። “እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፤ ብዙ ፍሬ የሚያፈራው በእኔ የሚኖርና እኔም በእርሱ የምኖርበት ነው፤ ነገር ግን ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም። በእኔ የማይኖር እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጪ ተጥሎ ይደርቃል፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ እሳት ይጣሉና ይቃጠላሉ። በእኔ ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የፈለጋችሁትን ብትለምኑ ታገኛላችሁ። ብዙ ፍሬ ስታፈሩ በዚህ አባቴ ይከብራል፤ እናንተም የእኔ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ታሳያላችሁ።

ዮሐንስ 15:1-8

ዮሐንስ 15:1-8 NASVዮሐንስ 15:1-8 NASV