ዮሐንስ 14:15-21

ዮሐንስ 14:15-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ከወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ኝስ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለ​ም​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከእ​ና​ንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽ​ናኝ ይል​ክ​ላ​ች​ኋል። እር​ሱም ዓለም ስለ​ማ​ያ​የ​ውና ስለ​ማ​ያ​ው​ቀው ሊቀ​በ​ለው የማ​ይ​ቻ​ለው የእ​ው​ነት መን​ፈስ ነው፤ እና​ንተ ግን ታው​ቁ​ታ​ላ​ችሁ፤ በእ​ና​ንተ ዘንድ ይኖ​ራ​ልና፤ ያድ​ር​ባ​ች​ሁ​ማ​ልና። “የሙት ልጆች ትሆኑ ዘንድ አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ። ገና ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ዓለም አያ​የ​ኝም፤ እና​ንተ ግን ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እና​ን​ተም ሕያ​ዋን ትሆ​ና​ላ​ችሁ። እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ፥ አብም በእኔ እን​ዳለ፥ እና​ን​ተም በእኔ፥ እኔም በእ​ና​ንተ እን​ዳ​ለሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። ትእ​ዛዜ በእ​ርሱ ዘንድ ያለ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውም የሚ​ወ​ደኝ እርሱ ነው፤ የሚ​ወ​ደ​ኝ​ንም አባቴ ይወ​ደ​ዋል፤ እኔም እወ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ራሴ​ንም እገ​ል​ጥ​ለ​ታ​ለሁ።”