ዮሐንስ 10:7-14

ዮሐንስ 10:7-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የበ​ጎች በር እኔ ነኝ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦ​ችና ወን​በ​ዴ​ዎች ናቸው፤ ነገር ግን፤ በጎች አል​ሰ​ሙ​አ​ቸ​ውም። እው​ነ​ተ​ኛዉ የበ​ጎች በር እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩ​ልም የሚ​ገባ ይድ​ናል፤ ይገ​ባ​ልም ይወ​ጣ​ልም፤ መሰ​ማ​ር​ያም ያገ​ኛል። ሌባ ግን ሊሰ​ር​ቅና ሊያ​ርድ፥ ሊያ​ጠ​ፋም ካል​ሆነ በቀር አይ​መ​ጣም፤ እኔ ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኙ፥ እጅ​ግም እን​ዲ​በ​ዛ​ላ​ቸው መጣሁ። “ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍ​ሱን ይሰ​ጣል። ጠባቂ ያይ​ደለ፥ በጎ​ቹም ገን​ዘቡ ያይ​ደሉ ምን​ደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎ​ቹን ትቶ ይሸ​ሻል፤ ተኵ​ላም መጥቶ በጎ​ችን ይነ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ልም። ምን​ደ​ኛስ ይሸ​ሻል፤ ስለ በጎ​ችም አያ​ዝ​ንም፤ ምን​ደኛ ነውና። ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትን መን​ጋ​ዎ​ችን አው​ቃ​ለሁ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትም ያው​ቁ​ኛል።