ኤርምያስ 43:1-2
ኤርምያስ 43:1-2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፥ ለእነርሱ አምላካቸው እግዚአብሔር የላከውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ መናገርን በፈጸመ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤ የኢዮስያስ ልጅ ኣዛርያስ፥ የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፥ “ሐሰት ተናግረሃል፤ አምላካችን እግዚአብሔር፦ በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብፅ አትግቡ ብሎ አልላከህም፤
ኤርምያስ 43:1-2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኤርምያስ፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ እንዲነግራቸው የላከውን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ለሕዝቡ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ፣ የሆሻያ ልጅ ዓዛርያስ፣ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና ትዕቢተኞች የሆኑ ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ትዋሻለህ! አምላካችን እግዚአብሔር፣ ‘እዚያ ለመኖር ወደ ግብጽ አትሂዱ ብለህ ንገራቸው’ ብሎ አልላከህም፤
ኤርምያስ 43:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፥ ለእነርሱ አምላካቸው እግዚአብሔር የላከውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ መናገርን በፈጸመ ጊዜ፥ የሆሻያ ልጅ ዓዛርያስ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፦ ሐሰት ተናግረሃል፥ አምላካችን እግዚአብሔር፦ በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብጽ አትግቡ ብሎ አልላከህም፥