ኤርምያስ 39:14
ኤርምያስ 39:14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኤርምያስንም ከግዞት ቤቱ አደባባይ አወጡት፤ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ እንዲህም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
ኤርምያስ 39:14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ልከው ኤርምያስን ከዘበኞች አደባባይ አስወጡት፤ የሳፋን ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወደ ቤቱ እንዲወስደው በዐደራ ሰጡት፤ ኤርምያስም በራሱ ሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
ኤርምያስ 39:14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኤርምያስንም ከግዞት ቤት አደባባይ አወጡት፥ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፥ እንዲህም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።