ኤርምያስ 32:6-15

ኤርምያስ 32:6-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ “እነሆ የአ​ጎ​ትህ የሰ​ሎም ልጅ አና​ም​ኤል ወደ አንተ መጥቶ፦ ትገ​ዛው ዘንድ የመ​ቤ​ዠቱ መብት የአ​ንተ ነውና በዓ​ና​ቶት ያለ​ውን እር​ሻ​ዬን ግዛ” ይል​ሃል። እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የአ​ጎቴ ልጅ አና​ም​ኤል እኔ ወደ አለ​ሁ​በት ወደ ግዞቱ ቤት አደ​ባ​ባይ መጥቶ፥ “በብ​ን​ያም ሀገር በዓ​ና​ቶት ያለ​ውን እር​ሻ​ዬን ግዛ፤ የመ​ግ​ዛ​ትና የመ​ው​ረስ መብቱ የአ​ንተ ነውና፥ አንተ ታላ​ቃ​ችን ነህና፤ ለአ​ንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ። በዐ​ና​ቶ​ትም ያለ​ውን እርሻ ከአ​ጎቴ ልጅ ከአ​ና​ም​ኤል ገዛሁ፤ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘ​ን​ሁ​ለት። የው​ሉ​ንም ወረ​ቀት ጻፍሁ፤ አተ​ም​ሁ​ትም፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ጠርቼ ብሩን በሚ​ዛን መዘ​ን​ሁ​ለት። የታ​ተ​መ​ው​ንም የውል ወረ​ቀት ወሰ​ድሁ፤ የአ​ጎ​ቴም ልጅ አና​ም​ኤል፥ የው​ሉ​ንም ወረ​ቀት የፈ​ረሙ ምስ​ክ​ሮች፥ በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ የተ​ቀ​መጡ አይ​ሁ​ድም ሁሉ እያዩ የው​ሉን ወረ​ቀት ለማ​ሴው ልጅ ለኔ​ርያ ልጅ ለባ​ሮክ ሰጠ​ሁት። በፊ​ታ​ቸ​ውም እን​ዲህ ብዬ ባሮ​ክን አዘ​ዝ​ሁት፦ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ይጠ​በቅ ዘንድ የታ​ተ​መ​ውን ይህን የውል ወረ​ቀት ወስ​ደህ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ አኑ​ረው። የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት​ንና እር​ሻን የወ​ይን ቦታ​ንም እንደ ገና ይገ​ዛሉ።”

ኤርምያስ 32:6-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኤርምያስም “የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ አለ፦ የአጎትህ የሰሎም ልጅ አናምኤል ወደ አንተ መጥቶ፣ ‘የመቤዠት መብት የአንተ ስለ ሆነ፣ በዓናቶት ያለውን መሬቴን ግዛኝ’ ይልሃል። “እግዚአብሔርም እንደ ተናገረኝ፣ የአጎቴ ልጅ አናምኤል ወደ ዘብ ጠባቂዎቹ አደባባይ መጥቶ፣ ‘የመቤዠቱን ርስት የማድረጉ መብት የአንተ ስለ ሆነ፣ በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን መሬቴን ለራስህ እንዲሆን ግዛው’ አለኝ።” ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወቅሁ፤ ስለዚህ በዓናቶት ያለውን መሬት ከአጎቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፤ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብር መዝኜ ሰጠሁት። በውሉም ሰነድ ላይ ፈረምሁ፤ አሸግሁትም። ብሩንም በምስክሮች ፊት በሚዛን መዘንሁለት። የስምምነቱ ዝርዝር ያለበትን፣ የታሸገውንና ያልታሸገውን የግዥውን የውል ሰነድ ወሰድሁ፤ በአጎቴም ልጅ በአናምኤልና በውሉ ላይ በፈረሙት ምስክሮች ፊት እንዲሁም በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ ተቀምጠው በነበሩ አይሁድ ሁሉ ፊት ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት። በእነርሱ ፊት ለባሮክ እንዲህ የሚል ትእዛዝ ሰጠሁት፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የታሸገውንና ያልታሸገውን፣ ሁለቱን የግዥ ውል ሰነዶች ለብዙ ጊዜ ሳይበላሹ እንዲቈዩ ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው። የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት፣ የዕርሻ ቦታና የወይን አትክልት ስፍራ እንደ ገና ይገዛሉ።’

ኤርምያስ 32:6-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ኤርምያስም እንዲህ አለ፦ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ እነሆ፥ የአጐትህ የሰሎም ልጅ አናምኤል ወደ አንተ መጥቶ፦ ትገዛው ዘንድ መቤዠቱ የአንተ ነውና በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ ይልሃል። እንደ እግዚአብሔርም ቃል የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፦ በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፥ እባክህ፥ ግዛ፥ ርስቱ የአንተ ነውና፥ መቤዠቱም የአንተ ነውና፥ ለአንተ ግዛው አለኝ። ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ አወቅሁ። በዓናቶትም ያለውን እርሻ ከአጐቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፥ አሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘንሁለት። በውሉም ወረቀት ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፥ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት። የታተመውንና የተከፈተውን የውል ወረቀት ወሰድሁ፥ የአጐቴም ልጅ አናምኤል፥ የውሉንም ወረቀት የፈረሙ ምስክሮች፥ በግዞትም ቤት አደባባይ የተቀመጡ አይሁድ ሁሉ እያዩ የውሉን ወረቀት ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት። በፊታቸውም እንዲህ ብዬ ባሮክን አዘዝሁት፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ይጠበቁ ዘንድ የታተመውንና የተከፈተውን ይህን የውል ወረከት ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህች ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።

ኤርምያስ 32:6-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እንደገናም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “አጐትህ የሻሉም ልጅ ሐናምኤል በብንያም ክፍል በዐናቶት የሚገኘውን መሬቱን እንድትገዛው ለመጠየቅ ወደ አንተ ይመጣል፤ የቅርብ ዘመድ ስለ ሆንክ ያን መሬት መግዛት የሚገባህ አንተ ነህ።” እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሐናምኤል ታስሬ ወዳለሁበት ወደ ዘብ ጠባቂዎች ክፍል መጥቶ “የመግዛት መብት ያንተ ስለ ሆነ መሬቴን ግዛ” አለኝ፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር እንደ ተናገረኝ ዐወቅሁ። መሬቱንም ከሐናምኤል ለመግዛት ገንዘቡን መዘንኩለት፤ የዋጋውም ልክ ወደ ሁለት ኪሎ የሚመዝን ብር ሆነ። የግዢውንም ውል ምስክሮች ባሉበት ፈርሜ አሸግሁት፤ ገንዘቡንም በሚዛን መዝኜ ሰጠሁት። ከዚያም አጠቃሎ ይዞ የታተመውንና ያልታተመውን የሽያጩን ውል ሁለት ግልባጭ ወስጄ፥ የማሕሴያ የልጅ ልጅ ለሆነው ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት፤ እነዚያን ግልባጮች የሰጠሁት በሐናምኤል፥ የሽያጩን ውል በፈረሙት ምስክሮችና በአደባባዩ ተቀምጠው በነበሩት ሰዎች ፊት ነው፤ በእነርሱም ሁሉ ፊት ባሮክን እንዲህ አልኩት፥ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የታሸገውንና ግልጥ የሆነውን ሁለቱንም የሽያጭ ውል ወረቀት ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ እንድታኖረውና ለብዙ ዘመን ተጠብቆ እንዲኖር አድርግ፤’ እንደገና በዚህች ምድር ቤቶችን፥ የእርሻ መሬቶችን፥ የወይን ተክል ቦታዎችን መግዛት የሚቻልበት ጊዜ ይመጣል ብሎአል።”

ኤርምያስ 32:6-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኤርምያስም እንዲህ አለ፦ “የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ እነሆ፥ የአጐትህ የሰሎም ልጅ አናምኤል ወደ አንተ መጥቶ፦ ‘በመግዛት የመቤዠት መብት የአንተ ነውና በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ’ ይልሃል። እንደ ጌታም ቃል የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፦ ‘በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፥ እባክህ፥ ግዛ፤ የርስቱና የመቤዠቱ መብት የአንተ ነውና፤ ለአንተ ግዛው’ አለኝ። ይህም የጌታ ቃል እንደሆነ አወቅሁ። በዓናቶትም ያለውን እርሻ ከአጐቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፥ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘንሁለት። በውሉም ሰነድ ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፥ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት። የተገዛበትን የውሉን ዝርዝር ሁኔታና ደንብ የያዘውን የታተመውን የውል ሰነድ እንዲሁም ካልታተመው ግልባጭ ጋር ወሰድሁ፤ የአጐቴም ልጅ አናምኤል፥ የተገዛበትን የውሉን ሰነድ የፈረሙት ምስክሮች፥ በእስርም ቤት አደባባይ የተቀመጡት አይሁድ ሁሉ እያዩ የተገዛበትን የውሉን ሰነድ ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት። በፊታቸውም እንዲህ ብዬ ባሮክን አዘዝሁት፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ተጠብቀው እንዲቆዩ የታተመውን ይህን የተገዛበትን የውል ሰነድና ካልታተመው የውል ሰነድ ጋር በአንድ ላይ ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህች ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደገና ይገዛሉ።’”