ኤርምያስ 17:7-8
ኤርምያስ 17:7-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ነገር ግን በእግዚአብሔር የሚታመን፣ መታመኛውም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውሃ ዳር እንደ ተተከለ፣ ሥሩንም ወደ ወንዝ እንደ ሰደደ ዛፍ ነው፣ ሙቀት ሲመጣ አይፈራም፤ ቅጠሉም ዘወትር እንደ ለመለመ ነው፤ በድርቅ ዘመን አይሠጋም፤ ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።”
ኤርምያስ 17:7-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በእግዚአብሔር የሚታመን፥ ተስፋውም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።
ኤርምያስ 17:7-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ነገር ግን በእግዚአብሔር የሚታመን፣ መታመኛውም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውሃ ዳር እንደ ተተከለ፣ ሥሩንም ወደ ወንዝ እንደ ሰደደ ዛፍ ነው፣ ሙቀት ሲመጣ አይፈራም፤ ቅጠሉም ዘወትር እንደ ለመለመ ነው፤ በድርቅ ዘመን አይሠጋም፤ ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።”
ኤርምያስ 17:7-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።
ኤርምያስ 17:7-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“በእኔ ብቻ ተማምኖ የሚኖር ሰው ግን የተባረከ ነው። እርሱም በወራጅ ምንጭ አጠገብ እንደ ተተከለና በውሃም ውስጥ ሥር እንደ ሰደደ ዛፍ ይሆናል፤ ዘወትር ቅጠሉ ለምለም ሆኖ የሚኖር ይህ ዐይነቱ ዛፍ የፀሐይ ሐሩር እንኳ አያሰጋውም፤ ዝናብ ባይዘንብለትም እንኳ ፍሬ ከማፍራት አይገታም።