መሳፍንት 7:1-22

መሳፍንት 7:1-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጌዴ​ዎን የተ​ባ​ለ​ውም ይሩ​በ​ኣል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ማል​ደው ተነሡ፤ በአ​ሮ​ኤድ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ነ​ርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረ​ብታ አጠ​ገብ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከአ​ንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝ​ቶ​አል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል፦ እጄ አዳ​ነኝ ብሎ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ይ​ብኝ እኔ ምድ​ያ​ምን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሁን እን​ግ​ዲህ፥ “የፈራ፥ የደ​ነ​ገ​ጠም ከገ​ለ​ዓድ ተራራ ተነ​ሥቶ ይመ​ለስ ብለህ በሕ​ዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕ​ዝ​ቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመ​ለሱ፤ ዐሥ​ርም ሺህ ቀሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ሕዝቡ ገና ብዙ ነው፤ ወደ ውኃ አው​ር​ዳ​ቸው፤ በዚ​ያም እፈ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ የም​ለው እርሱ ከአ​ንተ ጋር ይሄ​ዳል፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር አይ​ሂድ የም​ለው እርሱ አይ​ሄ​ድም” አለው። ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ውኃ አወ​ረደ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ውሻ እን​ደ​ሚ​ጠጣ ውኃ በም​ላሱ የሚ​ጠ​ጣ​ውን ሁሉ፥ እር​ሱን ለብ​ቻው አድ​ር​ገው፤ እን​ዲ​ሁም ሊጠጣ በጕ​ል​በቱ የሚ​ን​በ​ረ​ከ​ከ​ውን ሁሉ ለብ​ቻው አድ​ር​ገው” አለው። በእ​ጃ​ቸ​ውም ውኃ ወደ አፋ​ቸው አድ​ር​ገው የጠ​ጡት ቍጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀ​ሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጕ​ል​በ​ታ​ቸው ተን​በ​ረ​ከኩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “በእ​ጃ​ቸው ውኃ በጠ​ጡት በሦ​ስት መቶ ሰዎች አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ ምድ​ያ​ም​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የቀ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍ​ራ​ቸው ይመ​ለሱ” አለው። የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስን​ቅና ቀንደ መለ​ከት በእ​ጃ​ቸው ወሰዱ፤ የቀ​ሩ​ት​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ሰደ​ዳ​ቸው፤ ሦስ​ቱን መቶ ሰዎች ግን በእ​ርሱ ዘንድ ጠበ​ቃ​ቸው፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ርሱ በታች በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ። በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሰፈር ውረድ። ብቻ​ህ​ንም ለመ​ው​ረድ ብት​ፈራ አንተ ከሎ​ሌህ ፋራን ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤ የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም አድ​ም​ጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ እጆ​ችህ ይበ​ረ​ታሉ፤ ወደ ሰፈ​ርም ትወ​ር​ዳ​ለህ” አለው። እር​ሱም ከሎ​ሌው ፋራን ጋር ከሰ​ፈሩ በአ​ንድ ወገን የአ​ምሳ አለቃ ጦር ወደ ሰፈ​ረ​በት ወረደ። ብዛ​ታ​ቸ​ውም እንደ አን​በጣ የሆነ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን የም​ሥ​ራ​ቅም ልጆች ሁሉ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ሰፍ​ረው ነበር፤ የግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ብዛት ቍጥር እን​ደ​ሌ​ለው በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ነበረ። ጌዴ​ዎ​ንም በደ​ረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕል​ምን ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ሲያ​ጫ​ውት፥ “እነሆ፥ ሕልም አለ​ምሁ፤ እነ​ሆም፥ አን​ዲት የገ​ብስ እን​ጎቻ ወደ ምድ​ያም ሰፈር ተን​ከ​ባ​ልላ ወረ​ደች፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ደርሳ እስ​ኪ​ወ​ድቅ ድረስ መታ​ችው፤ ገለ​በ​ጠ​ች​ውም፤ ድን​ኳ​ኑም ወደቀ” ይል ነበር። ባል​ን​ጀ​ራ​ውም መልሶ፥ “ይህ ነገር ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰው ከኢ​ዮ​አስ ልጅ ከጌ​ዴ​ዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ያ​ም​ንና ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ በእጁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አል” አለው። ጌዴ​ዎ​ንም ሕል​ሙ​ንና ትር​ጓ​ሜ​ዉን በሰማ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር ተመ​ልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን ሠራ​ዊት በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና ተነሡ” አለ። ሦስ​ቱ​ንም መቶ ሰዎች በሦ​ስት ወገን ከፈ​ላ​ቸው፤ በሁ​ሉም እጅ ቀንደ መለ​ከ​ትና ባዶ ማሰሮ፥ በማ​ሰ​ሮ​ዉም ውስጥ ችቦ ሰጣ​ቸው። እር​ሱም፥ “እኔን ተመ​ል​ከቱ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርጉ፤ እነ​ሆም፥ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በደ​ረ​ስሁ ጊዜ እኔ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ እን​ዲሁ እና​ንተ አድ​ርጉ፤ እኔ ከእ​ኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለ​ከት ስን​ነፋ፥ እና​ንተ ደግሞ በሰ​ፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለ​ከ​ታ​ች​ሁን ንፉ፦ ኀይል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ሰይፍ የጌ​ዴ​ዎን በሉ” አላ​ቸው። ጌዴ​ዎ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት መቶ ሰዎች በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው ትጋት መጀ​መ​ሪያ ዘብ ጠባ​ቂ​ዎች ሳይ​ነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ች​ንም ነፉ፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ማሰ​ሮ​ዎች ሰባ​በሩ፤ ሦስ​ቱም ወገ​ኖች ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ነፉ፤ ማሰ​ሮ​ዎ​ች​ንም ሰበሩ፤ በግራ እጃ​ቸ​ውም ችቦ​ዎ​ችን፥ በቀኝ እጃ​ቸ​ውም ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ይዘው እየ​ነፉ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና የጌ​ዴ​ዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ። ሁሉም በየ​ቦ​ታው፥ በሰ​ፈሩ ዙሪያ ቆመ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ደን​ግ​ጠው ሸሹ። ሦስ​ቱ​ንም መቶ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ነፉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ውን ሁሉ ሰይፍ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ዉና በሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ላይ አደ​ረገ፤ ሠራ​ዊ​ቱም በጽ​ሬራ በኩል እስከ ቤት​ሲጣ ጋራ​ጋታ ድረስ በጣ​ባት አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ አቤ​ል​ሜ​ሁላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ።

መሳፍንት 7:1-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን፣ ከርሱም ጋራ የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጧት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተሰሜን በኩል፣ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበር። እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “ምድያማውያንን በእጃቸው አሳልፌ እንዳልሰጥ ዐብረውህ ያሉት ሰዎች በጣም ብዙ ናቸው፤ እስራኤላውያን የገዛ ኀይላቸው እንዳዳናቸው በመቍጠር እንዳይታበዩብኝ፣ ‘ማንም የፈራ ቢኖር የገለዓድን ተራራ ትቶ ወደ መጣበት ይመለስ’ ብለህ ለሕዝቡ ዐውጅ።” ስለዚህ ሃያ ሁለቱ ሺሕ ሲመለሱ ዐሥሩ ሺሕ ብቻ ቀሩ። እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “አሁንም ሰዎቹ ብዙ ናቸው፤ ወደ ወንዝ ይዘሃቸው ውረድ፤ በዚያም እለይልሃለሁ። ‘ይህ ከአንተ ጋራ ይሂድ’ የምለው፣ ከአንተ ጋራ ይሄዳል፤ ነገር ግን፣ ‘ይህ ከአንተ ጋራ አይሂድ’ የምለው፣ ከአንተ ጋራ አይሄድም።” ስለዚህ ጌዴዎን ሰዎቹን ወደ ወንዝ ይዟቸው ወረደ፤ እዚያም እግዚአብሔር፣ “ውሻ በምላሱ እየጨለፈ እንደሚጠጣ ሁሉ፣ በምላሳቸው የሚጠጡትን፣ በጕልበታቸው ተንበርክከው ከሚጠጡት ለይ” አለው። ሦስት መቶ ሰዎች ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ ጠጡ፤ የቀሩት ሁሉ ግን ለመጠጣት በጕልበታቸው ተንበረከኩ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፣ “ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ በጠጡት ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የቀሩት በሙሉ ወደ የመጡበት ይመለሱ” አለው። ጌዴዎንም የቀሩትን እስራኤላውያን በሙሉ ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ አደረገ፤ ሦስት መቶውን ግን አስቀራቸው፤ እነርሱም የሚመለሱትን ሰዎች ስንቅና መለከት ወሰዱ። በዚህ ጊዜ የምድያማውያኑ ሰፈር ከእነርሱ በታች በሸለቋማው ውስጥ ነበር። በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “ተነሥ፤ በሰፈሩም ላይ ውረድ፤ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁና። አደጋ ለመጣል የምትፈራ ከሆነ ግን፣ ፉራ ከተባለው አገልጋይህ ጋራ ወደ ሰፈሩ ውረድ፤ የሚሉትንም ስማ፤ ከዚያ በኋላ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ።” ስለዚህም ጌዴዎን አገልጋዩን ፉራን አስከትሎ እስከ ሰፈሩ ዳርቻ ወረደ። ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም። አንድ ሰው ያየውን ሕልም ለጓደኛው በሚነግርበት ጊዜ ጌዴዎን እዚያ ደረሰ። ያም ሰው፣ “በሕልሜ ክብ የሆነ አንድ የገብስ ቂጣ ከላይ ተንከባሎ በምድያማውያን ሰፈር ላይ ሲወርድ፣ ድንኳኑንም ሲመታው ከአመታቱም ኀይለኛነት የተነሣ ድንኳኑ ተገልብጦ ሲፈራርስ አየሁ” በማለት ይነግረው ነበር። ጓደኛውም መልሶ፣ “ይህ የእስራኤላዊው የኢዮአስ ልጅ የጌዴዎን ሰይፍ እንጂ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድያማውያንንና ሰፈሩን በሙሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶታልና” አለው። ጌዴዎንም ሕልሙንና ፍችውን በሰማ ጊዜ ሰገደ፤ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ወጥቶ፣ “እግዚአብሔር የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷልና ተነሡ” አላቸው። ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፣ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ። ጌዴዎንም እንዲህ አላቸው፤ “እኔን ተመልከቱ፤ የማደርገውንም አድርጉ፤ በሰፈሩ ዳርቻ ስደርስ እኔ የማደርገውን አይታችሁ ልክ እንደዚያው አድርጉ። እኔና ዐብረውኝ ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከቶቻችንን በምንነፋበት ጊዜ እናንተም በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለከቶቻችሁን እየነፋችሁ፣ ‘ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን’ ብላችሁ ጩኹ።” ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፣ ጌዴዎንና ዐብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮዎች ሰበሩ። በሦስት ቡድን የተከፈሉት ሰዎች ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ ማሰሮዎቻቸውንም ሰበሩ፤ ችቦዎቻቸውን በግራ እጆቻቸው፣ የሚነፏቸውንም ቀንደ መለከቶች በቀኝ እጆቻቸው ይዘው፣ “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ” በማለት ጮኹ። እያንዳንዱ ሰው በሰፈሩ ዙሪያ የተመደበበትን ቦታ እንደ ያዘም ምድያማውያኑ እየጮኹ ሸሹ። የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደ ተሰማም እግዚአብሔር በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሰራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ ወደ ቤትሺጣ፣ ከዚያም ዐልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ።

መሳፍንት 7:1-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ጌዴዎን የተባለውም ይሩበኣል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፥ በሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ፥ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም። አሁንም እንግዲህ፦ የፈራ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ አለው። ከሕዝቡም ሀያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፥ አሥርም ሺህ ቀሩ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ሕዝቡ ገና ብዙ ነው፥ ወደ ውኃ አውርዳቸው፥ በዚያም እፈትናቸዋለሁ፥ እኔም፦ ይህ ከአንተ ጋር ይሂድ የምለው እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፥ እኔም፦ ይህ ከአንተ ጋር አይሂድ የምለው እርሱ አይሄድም አለው። ሕዝቡንም ወደ ውኃ አወረደ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ውሻ እንደሚጠጣ ውኃ በምላሱ የሚጠጣውን ሁሉ፥ እርሱን ለብቻው አድርገው፥ እንዲሁም ሊጠጣ በጉልበቱ የሚንበረከከውን ሁሉ ለብቻው አድርገው አለው። በእጃቸውም ውኃ ወደ አፋቸው አድርገው የጠጡት ቁጥር ሦስት መቶ ነበረ፥ የቀሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጉልበታቸው ተንበረከኩ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ በእጃቸው ውኃ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፥ ምድያማውያንንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፥ የቀሩት ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍራቸው ይመለሱ አለው። የሕዝቡንም ስንቅና ቀንደ መለከት በእጃቸው ወሰዱ፥ የቀሩትንም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ድንኳናቸው ሰደዳቸው፥ ሦስቱን መቶ ሰዎች ግን በእርሱ ዘንድ ጠበቃቸው፥ የምድያምም ሰፈር ከእርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበረ። በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር፦ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻቸዋለሁና ተነሥተህ ወደ ሰፈር ውረድ። አንተም ለመውረድ ብትፈራ አንተ ከሎሌህ ከፉራ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፥ የሚናገሩትንም ትሰማለህ፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትወርድ ዘንድ እጅህ ትበረታለች አለው። እርሱና ሎሌው ፉራ በሰፈሩ ዳርቻ ወደ ነበሩት ሰልፈኞች ወረዱ። ብዛታቸውም እንደ አንበጣ የሆነ ምድያማውያንና አማሌቃውያን የምሥራቅም ሰዎች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፥ የግመሎቻቸውም ብዛት ቁጥር እንደሌለው በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበረ። ጌዴዎንም በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕልምን ለባልንጀራው ሲያጫውት፦ እነሆ፥ ሕልም አለምሁ፥ እነሆም፥ አንዲት የገብስ እንጎቻ ወደ ምድያም ሰፈር ተንከባልላ ወረደች፥ ወደ ድንኳኑም ደርሳ እስኪወድቅ ድረስ መታችው፥ ገለበጠችውም፥ ድንኳኑም ተጋደመ ይል ነበር። ባልንጀራውም መልሶ፦ ይህ ነገር ከእስራኤል ሰው ከኢዮአስ ልጅ ከጌዴዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይደለም፥ እግዚአብሔር ምድያምንና ሠራዊቱን ሁሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶአል አለው። ጌዴዎንም ሕልሙንና ትርጓሜውን በሰማ ጊዜ ሰገደ፥ ወደ እስራኤልም ሰፈር ተመልሶ፦ እግዚአብሔር የምድያምን ሠራዊት በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ አለ። ሦስቱንም መቶ ሰዎች በሦስት ወገን ከፈላቸው፥ በሁሉም እጅ ቀንደ መለከትና ባዶ ማሰሮ፥ በማሰሮውም ውስጥ ችቦ ሰጠ። እርሱም፦ እኔን ተመልከቱ፥ እንዲሁም አድርጉ፥ እነሆም፥ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በደረስሁ ጊዜ እኔ እንደማደርግ እንዲሁ እናንተ አድርጉ፥ እኔ ከእኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከት ስንነፋ፥ እናንተ ደግሞ በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለከታችሁን ንፉ፦ ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን በሉ አላቸው። ጌዴዎንም ከእርሱም ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች በመካከለኛው ትጋት ትጋቱም በተጀመረ ጊዜ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፥ ቀንደ መለከቶችንም ነፉ፥ በእጃቸውም የነበሩትን ማሰሮች ሰባበሩ። ሦስቱም ወገኖች ቀንደ መለከቶችን ነፉ፥ ማሰሮችንም ሰበሩ፥ በግራ እጃቸውም ችቦችን፥ በቀኝ እጃቸውም ቀንደ መለከቶችን ይዘው እየነፉ፦ የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ ብለው ጮኹ። ሁሉም በየቦታው በሰፈሩ ዙሪያ ቆመ፥ ሠራዊቱም ሁሉ ሮጠ፥ ጮኸ፥ ሸሸም። ሦስቱንም መቶ ቀንደ መለከቶች ነፉ፥ እግዚአብሔርም የሰውን ሁሉ ሰይፍ በባልንጀራውና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ አደረገ፥ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሺጣ ድረስ በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ።

መሳፍንት 7:1-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በማግስቱም ማለዳ ይሩባዓል የተባለው ጌዴዎንና ተከታዮቹ በጧት ማልደው ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያን ሰፈርም ከእነርሱ በስተሰሜን በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆ ውስጥ ነበር። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “በምድያማውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው ዘንድ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች ለእኔ እጅግ ብዙ ሆነዋል፤ በራሳቸው ኀይል የሚያሸንፉ ስለሚመስላቸው ለእኔ ክብር ከመስጠት ይቈጠባሉ፤ ስለዚህ ለሕዝቡ ‘ከመካከላችሁ ፈሪና ድንጉጥ የሆነ ሰው ካለ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ እኛም በዚህ በገለዓድ ተራራ ላይ እንቈያለን’ ብለህ ንገራቸው።” በዚህ ምክንያት ኻያ ሁለቱ ሺህ ሲመለሱ ዐሥሩ ሺህ ቀሩ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “አሁንም ገና ብዙ ሠራዊት አሉህ፤ እነርሱን ወደ ወንዝ ውሰዳቸውና በዚያ እኔ እፈትናቸዋለሁ፤ ከአንተ ጋር ይሂድ የምለው ሰው ይሂድ፤ ይቅር የምለው ሰው ደግሞ ይመለስ።” ጌዴዎንም ሰዎቹን ወደ ወንዝ ውሃ አወረዳቸው፤ እግዚአብሔርም “በጒልበቱ ተንበርክኮ ውሃ ከሚጠጣው መካከል እንደ ውሻ በምላሱ እየጨለፈ የሚጠጣውን ሁሉ ለየው!” አለው። በእጃቸው ውሃ እየዘገኑ የሚጠጡት ቊጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀሩት ሁሉ የጠጡት ግን በጒልበታቸው ተንበርክከው ነበር። እግዚአብሔር ጌዴዎንን “በእጃቸው ውሃ እየዘገኑ በጠጡት በእነዚህ ሦስት መቶ ሰዎች አማካይነት አድናችኋለሁ፤ በምድያማውያን ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርግሃለሁ፤ ለቀሩት ግን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ንገራቸው” አለው። ስለዚህ ጌዴዎን የሕዝቡን ስንቅና እምቢልታዎቹን ከተረከቡት ከሦስት መቶዎቹ በቀር ሌሎቹን እስራኤላውያን ሁሉ ወደየቤታቸው እንዲመለሱ አሰናበታቸው፤ ይህም ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ የምድያማውያን ሰፈር ከእነርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበር። በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፥ “በእነርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ የማደርግህ ስለ ሆነ ተነሥተህ የእነርሱን ሰፈር አጥቃ። አንተ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ከፈራህ ግን ፑራ ተብሎ ከሚጠራው አገልጋይህ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤ እነርሱም የሚሉትን ትሰማለህ፤ ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤”። ስለዚህ ጌዴዎንና አገልጋዩ ፑራ ወደ ጠላት ሰፈር ዳርቻ ወረዱ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ ዐማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ ግመሎቻቸውም ከብዛታቸው የተነሣ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ሊቈጠር የማይቻል ነበር። ጌዴዎን እዚያ በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ያየውን ሕልም ለጓደኛው ሲነግረው ሰማ፤ ሕልሙም እንዲህ የሚል ነበር፦ “አንዲት የገብስ ቂጣ ከላይ ተንከባልላ ወርዳ ወደ ምድያም ሰፈር ደርሳ በዚያ ያለውን ድንኳን መታችው፤ ድንኳኑም ተገልብጦ በምድር ላይ ተዘረጋ።” ጓደኛውም “ይህማ የእስራኤላዊው የኢዮአስ ልጅ የጌዴዎን ሰይፍ ነው! ከቶ ሌላ ትርጒም ሊሰጠው አይችልም፤ እግዚአብሔር ለጌዴዎን በምድያምና በመላው ሠራዊታችን ላይ ድልን ሰጥቶታል!” ሲል መለሰለት። ጌዴዎን ስለ ሰውየው ሕልምና ስለ ፍቹም ምንነት በሰማ ጊዜ በጒልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤላውያንም ሰፈር ተመልሶ “እግዚአብሔር በምድያማውያንና በሠራዊቱ ላይ ድልን የሚያቀዳጃችሁ ስለ ሆነ ተነሡ!” አላቸው። ሦስት መቶዎቹንም ሰዎች ከፍሎ በሦስት ቡድን መደባቸው፤ ለእያንዳንዱም ሰው አንድ እምቢልታና በውስጡ ችቦ ያለበት አንድ ማሰሮ ሰጠ። እንዲህም አላቸው፤ “እኔ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ ስደርስ፥ የማደርገውን በጥንቃቄ ተመልክታችሁ ያንኑ አድርጉ። እኔና ከእኔ ጋር የተመደቡት ሰዎች በቀንደ መለከቶቻችን ድምፅ ስናሰማ፥ እናንተም የራሳችሁን እምቢልታ ድምፅ በሰፈሩ ዙሪያ እያሰማችሁ ‘ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን ተዋጉ!’ ብላችሁ ጩኹ።” ከእኩለሌሊት ጥቂት ቀደም ብሎ፥ ዘብ ጠባቂዎች ከተቀያየሩ በኋላ ጌዴዎንና ከእርሱ ጋር የተመደቡት መቶ ሰዎች ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ እምቢልታዎቻቸውን ነፉ፤ የያዙትንም ማሰሮ ሁሉ ሰባበሩ። በሌላም በኩል የነበሩት ሁለቱ ክፍሎች እንዲሁ አደረጉ፤ ሁሉም የተለኰሱትን ችቦዎቻቸውን በግራ እጃቸው፥ እምቢልታቸውን በቀኝ እጃቸው ይዘው “ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን እንዋጋለን!” እያሉ በመጮኽ ደነፉ። እያንዳንዱ ሰው በሰፈሩ ዙሪያ በተመደበለት ቦታ ቆመ፤ መላው የጠላት ሠራዊትም የኡኡታ ድምፅ እያሰማ ሸሸ፤ ሦስት መቶው የጌዴዎን ሰዎች እምቢልታቸውን በሚነፉበት ጊዜ እግዚአብሔር እያንዳንዱን የጠላት ወታደር በጓደኛው ላይና በሠራዊቱ ላይ ሰይፉን እንዲያነሣ አደረገ፤ ሠራዊቱም ፊታቸውን ወደ ጽሬራ በመመለስ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፎ በጣባት አጠገብ እስካለው አቤልመሖላ ድረስ ሸሽተው ሄዱ።

መሳፍንት 7:1-22 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ይሩበኣል የተባለው ጌዴዎን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጠዋት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተ ሰሜን በኩል፥ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ። ጌታም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም። አሁንም እንግዲህ፦ የፈራ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ አለው። ከሕዝቡም ሀያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፥ ዐሥርም ሺህ ቀሩ። ጌታ ጌዴዎንን እንዲህ አለው፥ “አሁንም ሰዎቹ ብዙ ናቸው፤ ወደ ወንዝ ይዘሃቸው ውረድ፤ በዚያም እጸልይልሃለሁ። ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሂድ’ የምለው፥ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ነገር ግን፥ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሂድ’ የምለው፥ ከአንተ ጋር አይሄድም።” ስለዚህ ጌዴዎን ሰዎቹን ወደ ወንዝ ይዞአቸው ወረደ፤ እዚያም ጌታ፥ “ውሻ በምላሱ እየጨለፈ እንደሚጠጣ ሁሉ፥ በምላሳቸው የሚጠጡትን፥ በጉልበታቸው ተንበርክከው ከሚጠጡት ለይ” አለው። ሦስት መቶ ሰዎች ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ ጠጡ፤ የቀሩት ሁሉ ግን ለመጠጣት በጉልበታቸው ተንበረከኩ። ጌታም ጌዴዎንን፥ “ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ በጠጡት ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችሃለሁ፤ የቀሩት በሙሉ ወደየመጡበት ይመለሱ” አለው። ጌዴዎንም የቀሩትን እስራኤላውያን በሙሉ ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ አደረገ፤ ሦስት መቶውን ግን አስቀራቸው፤ እነርሱም የሚመለሱትን ሰዎች ስንቅና መለከት ወሰዱ። በዚህ ጊዜ የምድያማውያኑ ሰፈር ከእነርሱ በታች በሸለቆአማው ውስጥ ነበር። በዚያች ሌሊት ጌታ ጌዴዎንን እንዲህ አለው፥ “ተነሥ፤ በሰፈሩም ላይ ውረድ፤ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁና። አደጋ ለመጣል የምትፈራ ከሆነ ግን፥ ፉራ ከተባለው አገልጋይህ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤ የሚሉትንም አድምጥ፤ ከዚያ በኋላ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤” ስለዚህም ጌዴዎን አገልጋዩን ፉራን አስከትሎ እስከ ሰፈሩ ዳርቻ ወረደ። ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም። አንድ ሰው ያየውን ሕልም ለጓደኛው በሚነግርበት ጊዜ ጌዴዎን እዚያ ደረሰ። ያም ሰው፥ “በሕልሜ ክብ የሆነ አንድ የገብስ ቂጣ ከላይ ተንከባሎ በምድያማውያን ሰፈር ላይ ሲወርድ፥ ድንኳኑንም ሲመታው ከአመታተም ኀይለኛነት የተነሣድንኳኑ ተገልብጦ ሲፈራርስ አየሁ” በማለት ይነግረው ነበር። ጓደኛውም መልሶ፥ “ይህ የእስራኤላዊው የኢዮአስ ልጅ የጌዴዎን ሰይፍ እንጂ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድያማውያንንና ሰፈሩን በሙሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶታልና” አለው። ጌዴዎንም ሕልሙንና ፍቺውን በሰማ ጊዜ ለጌታ ሰገደ፤ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ወጥቶ፥ “ጌታ የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ!” አላቸው። ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፥ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ። ጌዴዎንም እንዲህ አላቸው፤ “እኔን ተመልከቱ፤ የማደርገውንም አድርጉ፤ በሰፈሩ ዳርቻ ስደርስ እኔ የማደርገውን አይታችሁ ልክ እንደዚያው አድርጉ። እኔና አብረውኝ ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከቶቻችንን በምንነፋበት ጊዜ እናንተም በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለከቶቻቸሁን እየነፋችሁ፥ ‘ለጌታና ለጌዴዎን’ ብላችሁ ጩኹ።” ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፥ ጌዴዎንና አብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮች ሰበሩ። በሦስት ቡድን የተከፈሉት ሰዎች ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ ማሰሮቻቸውንም ሰበሩ፤ ችቦዎቻቸውን በግራ እጆቻቸው፥ ቀንደ መለከቶቻቸውንም በቀኝ እጆቻቸው ይዘው፥ “የጌታና የጌዴዎን ሰይፍ” በማለት ጮኹ። እያንዳንዱ ሰው በሰፈሩ ዙሪያ የተመደበበትን ቦታ እንደያዘም ምድያማውያኑ እየጮሁ ሸሹ። የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደተሰማም ጌታ በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሠራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልመሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ።