መሳፍንት 4:8-9
መሳፍንት 4:8-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ባርቅም፥ “አንቺ ከእኔ ጋር ብትሄጂ እኔ እሄዳለሁ፤ አንቺ ግን ከእኔ ጋር ባትሄጂ እኔ አልሄድም፤ እግዚአብሔር መልአኩን ከእኔ ጋር የሚልክበትን ዕለት አላውቃትምና” አላት። ዲቦራም፥ “በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን በሴት እጅ አሳልፎ ይሰጣልና በዚህ በምትሄድበት መንገድ ለአንተ ክብር አይሆንም” አለችው። ዲቦራም ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች።
ያጋሩ
መሳፍንት 4 ያንብቡመሳፍንት 4:8-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ባርቅም፣ “ዐብረሽኝ የምትሄጂ ከሆነ እሄዳለሁ፤ ዐብረሽኝ የማትሄጂ ከሆነ ግን አልሄድም” አላት። ዲቦራ መልሳ፣ “ይሁን ዕሺ፤ መሄዱን ዐብሬህ እሄዳለሁ፤ በዚህ ሁኔታ የምትሄድ ከሆነ ግን ክብሩ ለአንተ አይሆንም፤ እግዚአብሔር ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና” አለችው። ስለዚህ ዲቦራ ከባርቅ ጋራ ወደ ቃዴስ ሄደች፤
ያጋሩ
መሳፍንት 4 ያንብቡመሳፍንት 4:8-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ባርቅም፦ አንቺ ከእኔ ጋር ብትሄጂ እኔ እሄዳለሁ፥ አንቺ ግን ከእኔ ጋር ባትሄጂ እኔ አልሄድም አላት። እርሷም፦ በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን በሴት እጅ አሳልፎ ይሰጣልና በዚህ በምትሄድበት መንገድ ለአንተ ክብር አይሆንም አለችው። ዲቦራም ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች።
ያጋሩ
መሳፍንት 4 ያንብቡ