መሳፍንት 3:1-2 - Compare All Versions

መሳፍንት 3:1-2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚህ ጊዜ በከነዓን ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተሳትፈው የማያውቁትን እስራኤላውያን ለመፈተን፣ እግዚአብሔር ባሉበት የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው፤ ይህን ማድረጉ ቀደም ሲል በጦር ሜዳ ውለው የማያውቁትን የእስራኤል ልጆች የጦርነት ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ ብቻ ነው፤

መሳፍንት 3:1-2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በከነዓን ምድር ጦርነት ያልተለማመዱ እስራኤላውያንን ለመፈተን እግዚአብሔር በምድሪቱ የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው። ይህንንም ማድረጉ ቀድሞ የጦርነት ልምድ ያልነበራቸውን የእስራኤልን ትውልድ የጦርነት ስልት ለማስተማር ብሎ ብቻ ነው።

መሳፍንት 3:1-2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ጦር​ነት ሁሉ ያላ​ወ​ቁ​ትን እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ነ​ርሱ ይፈ​ት​ና​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ተዋ​ቸው። ይህም ጦር​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ትው​ልድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት እነ​ዚ​ህን አላ​ወ​ቋ​ቸ​ውም ነበር፤

መሳፍንት 3:1-2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከከነዓናውያንም ጋር መዋጋት ያላወቁትን እስራኤልን በእነርሱ ይፈትናቸው ዘንድ፥ በፊትም ሰልፍን ያልለመዱ የእስራኤል ልጆች ትውልድ መዋጋትን ያውቁና ይማሩ ዘንድ እግዚአብሔር ያስቀራቸው አሕዛብ እነዚህ ናቸው፥

መሳፍንት 3:1-2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በዚህ ጊዜ በከነዓን ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተሳትፈው የማያውቁትን እስራኤላውያን ለመፈተን፥ ጌታ ባሉበት የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው። ይህን ማድረጉ ቀደም ሲል በጦር ሜዳ ውለው የማያውቁትን የእስራኤል ልጆች የጦርነት ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ ብቻ ነው።