መሳፍንት 21:17-18
መሳፍንት 21:17-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ደግሞም፥ “ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዳይደመሰስ ከብንያም ላመለጡት ርስት ይኑር። የእስራኤልም ልጆች፥ “ልጁን ለብንያም የሚሰጥ ርጉም ይሁን ብለው ምለዋልና እኛ ከልጆቻችን ሚስቶችን ለእነርሱ መስጠት አንችልም” አሉ።
መሳፍንት 21:17-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከእስራኤል ነገዶች አንዱ የሆነው እንዳይጠፋ አሁን በሕይወት ያሉት ብንያማውያን ወራሽ የሚሆን ዘር ሊኖራቸው ይገባል። ‘ልጁን ለብንያማዊ የሚድር ርጉም ይሁን’ ብለን እኛ እስራኤላውያን ስለ ተማማልን እንግዲህ ልጆቻችንን ልንድርላቸው አንችልም፤
መሳፍንት 21:17-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ደግሞም፦ ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዳይደመሰስ ከብንያም ላመለጡት ርስት ይኑር። የእስራኤልም ልጆች፦ ልጁን ለብንያም የሚድር ርጉም ይሁን ብለው ምለዋልና እኛ ልጆቻችንን ለእነርሱ ማጋባት አይሆንልንም አሉ።