መሳፍንት 2:7-9
መሳፍንት 2:7-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢያሱም በነበረበት ዘመን ሁሉ፥ ለእስራኤልም ያደረገውን ታላቁን የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ባወቁት፥ ከኢያሱ በኋላ በነበሩ ሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ተገዙ። የእግዚአብሔርም አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆነው ሞተ። በተራራማዉ በኤፍሬም ሀገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ዳርቻ በተምናሴራ ቀበሩት።
መሳፍንት 2:7-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ እንዲሁም ከርሱ በኋላ እግዚአብሔር ለእስራኤል ያደረገውን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ ያዩ አለቆች በነበሩበት ዘመን ሁሉ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አመለከ። የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ በመቶ ዐሥር ዓመቱ ሞተ። እነርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በምትገኘው ከገዓስ ተራራ በስተሰሜን ባለችው በራሱ ርስት ላይ በተምናሔሬስ ቀበሩት።
መሳፍንት 2:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢያሱም በነበረበት ዘመን ሁሉ፥ ለእስራኤልም ያደረገውን ታላቁን የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ባዩት፥ ከኢያሱ በኋላ በነበሩ ሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ፥ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አመለኩ። የእግዚአብሔርም ባሪያ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድሜው መቶ አሥር ዓመት ሲሆነው ሞተ። በተራራማውም በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ዳርቻ በተምናሔሬስ ቀበሩት።
መሳፍንት 2:7-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በኢያሱ ዘመንና በኋላ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ታላቅ ሥራ ባዩት ሽማግሌዎች የሕይወት ዘመን ሁሉ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አመለከ። የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆነው ሞተ፤ የራሱ ድርሻ በሆነውም ርስት ተቀበረ፤ ይህም እርሱ የተቀበረበት ምድር በኮረብታማው የኤፍሬም አገር ከጋዓሽ ተራራ በስተሰሜን የሚገኘውና “ቲምናት ሴራሕ” ተብሎ የሚጠራው ነው።