መሳፍንት 2:1-3

መሳፍንት 2:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከገ​ል​ገላ ወደ ቀላ​ው​ት​ም​ኖስ ወደ ቤቴል ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ወጥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቼ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ እሰ​ጣ​ች​ሁም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር አግ​ብ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም፦ ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አላ​ፈ​ር​ስም፤ እና​ን​ተም በዚች ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርጉ፤ ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸው፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ስበሩ፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ው​ንም አፍ​ርሱ አልሁ። እና​ንተ ግን ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ ይህ​ንስ ለምን አደ​ረ​ጋ​ችሁ? ስለ​ዚ​ህም እኔ አሕ​ዛ​ብን ከፊ​ታ​ችሁ አላ​ወ​ጣ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ያስ​ጨ​ን​ቋ​ች​ኋል፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወጥ​መድ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል” አልሁ።