መሳፍንት 13:2-7
መሳፍንት 13:2-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚባል አንድ የሶራሕ ሰው ነበረ፤ ሚስቱም መካን ነበረች፤ ልጅም አልወለደችም ነበር። የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅንና የሚያሰክር መጠጥንም አትጠጪ፤ ርኩስም ነገር አትብዪ። እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።” ሴቲቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደ መጣ ጠየቅሁት፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም። እርሱም፦ እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ እንግዲህ የወይን ጠጅንና የሚያሰክር መጠጥን አትጠጪ፥ ርኩስ ነገርንም አትብዪ፤ ልጁ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አለኝ” ብላ ተናገረች።
መሳፍንት 13:2-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ማኑሄ የተባለ ከዳን ወገን የተወለደ አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፤ ሚስቱ መካን ስለ ነበረች ልጅ አልወለደችም። የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። እንግዲህ ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገርም አትብዪ፤ ምክንያቱም ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ልጁ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለአምላክ የተለየ ይሆናልና፤ እስራኤልንም ከፍልስጥኤማውያን እጅ መታደግ ይጀምራል።” ከዚያም ሴቲቱ ወደ ባሏ ሄዳ እንዲህ አለችው፤ “የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ የሚመስልና እጅግ የሚያስደነግጥ ነበር። ከየት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤ ነገር ግን፣ ‘ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገር አትብዪ፤ ልጁም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና’ ብሎኛል።”
መሳፍንት 13:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፥ ሚስቱም መካን ነበረች፥ ልጅም አልወለደችም። የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፦ እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፥ ልጅም አልወለድሽም፥ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። አሁንም ተጠንቀቂ፥ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ። እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፥ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል። ሴቲቱም ወደ ባልዋ መጥታ፦ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፥ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፥ ከወዴትም እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም። እርሱም፦ እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አሁን የወይን ጠጅ የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ አለኝ ብላ ተናገረች።
መሳፍንት 13:2-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በዚያን ዘመን ጾርዓ በምትባል ከተማ የሚኖር ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከዳን ነገድ ነበር፤ ሚስቱ መኻን ስለ ነበረች ልጆች አልወለደችም፤ ለእርስዋም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “አንቺ መኻን ነሽ፤ ልጆችም የሉሽም፤ ነገር ግን ትፀንሺአለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ ከመጠጣትና ማንኛውንም ርኩስ ምግብ ከመብላት ተጠንቀቂ። በእርግጥ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን የራስ ጠጒሩን ፈጽሞ አይላጭ፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።” ከዚህ በኋላ ሴቲቱ መጥታ ለባልዋ እንዲህ አለችው፤ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጥቶ ነበር፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤ እኔ ከወዴት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤ ነገር ግን እርሱ ‘እነሆ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ’ ብሎ ነገረኝ፤ እንዲሁም የሚወለደው ልጅ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በናዝራዊነት ለእግዚአብሔር የተለየ ስለሚሆን፥ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ ከመጠጣትና ማንኛውንም ርኩስ ምግብ ከመብላት እንድጠነቀቅ ነግሮኛል።”
መሳፍንት 13:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ማኑሄ የተባለ ከዳን ወገን የተወለደ አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፤ ሚስተ መካን ስለ ነበረች ልጅ አልወለደችም። የጌታም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። እንግዲህ ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገርም አትብይ፤ ምክንያቱም ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ልጁ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና፤ እስራኤልንም ከፍልስጥኤማውያን እጅ መታደግ ይጀምራል።” ከዚያም ሴቲቱ ወደ ባሏ ሄዳ እንዲህ አለችው፤ “የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ የሚመስልና እጅግ የሚያስደነግጥ ነበር። ከየት እንደመጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤ ነገር ግን፥ ‘ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገር አትብይ፤ ልጁም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና’ ብሎኛል።”