መሳፍንት 13:18-20 - Compare All Versions

መሳፍንት 13:18-20 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ?” አለው። ማኑ​ሄም የፍ​የ​ሉን ጠቦ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ወስዶ በድ​ን​ጋይ ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​በው። መል​አ​ኩም ተአ​ም​ራት አደ​ረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ይመ​ለ​ከቱ ነበር። ነበ​ል​ባ​ሉም ከመ​ሠ​ዊ​ያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ ነበ​ል​ባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ተመ​ለ​ከቱ፤ በም​ድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ።

መሳፍንት 13:18-20 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የእግዚአብሔርም መልአክ፣ “ስሜ ድንቅ ስለ ሆነ፣ ለምን ትጠይቀኛለህ?” አለው። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቍርባኑ ጋራ ወስዶ በዐለት ላይ ለእግዚአብሔር ሠዋው። ማኑሄና ሚስቱ እያዩ እግዚአብሔር አስደናቂ ነገር አደረገ፤ ይኸውም የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ዐረገ። ማኑሄና ሚስቱ ይህን ሲመለከቱ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።

መሳፍንት 13:18-20 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የእግዚአብሔርም መልአክ፦ ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ? አለው። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቁርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም ተአምራት አደረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም ይመለከቱ ነበር። ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፥ በምድርም በግምባራቸው ተደፉ።

መሳፍንት 13:18-20 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

መልአኩም “ስሜን ለማወቅ የፈለግኸው ለምንድን ነው? ስሜ ድንቅ ነው” ሲል መለሰለት። ከዚህ በኋላ ማኑሄ አንድ የፍየል ጠቦትና የእህል ቊርባን ወስዶ በአለቱ መሠዊያ ላይ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ ማኑሄና ሚስቱም እየተመለከቱ ሳለ እግዚአብሔር አስደናቂ ነገር አደረገ። ነበልባሉ ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ ማኑሄና ሚስቱ እየተመለከቱ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ሆኖ ወደ ላይ ወጣ፤ እነርሱም በግንባራቸው በመሬት ላይ ተደፉ።

መሳፍንት 13:18-20 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

የጌታም መልአክ፥ “ስሜ ድንቅ ስለ ሆነ፥ ለምን ትጠይቀኛለህ?” አለው። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቁርባኑ ጋር ወስዶ በዐለት ላይ ለጌታ ሠዋው። ማኑሄና ሚስቱ እያዩ ጌታ አስደናቂ ነገር አደረገ፤ የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ፥ የጌታ መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ዐረገ። ማኑሄና ሚስቱ ይህን ሲመለከቱ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።