መሳፍንት 13:1-25

መሳፍንት 13:1-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አርባ ዓመት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚ​ባል አንድ የሶ​ራሕ ሰው ነበረ፤ ሚስ​ቱም መካን ነበ​ረች፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ደ​ችም ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለሴ​ቲቱ ተገ​ልጦ እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ድ​ሽም፤ ነገር ግን ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ። አሁ​ንም ተጠ​ን​ቀቂ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥ​ንም አት​ጠጪ፤ ርኩ​ስም ነገር አት​ብዪ። እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ልጁም ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና በራሱ ላይ ምላጭ አይ​ድ​ረ​ስ​በት፤ እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ማዳን ይጀ​ም​ራል።” ሴቲ​ቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መል​ኩም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ነበረ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ መጣ ጠየ​ቅ​ሁት፥ እር​ሱም ስሙን አል​ነ​ገ​ረ​ኝም። እር​ሱም፦ እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ እን​ግ​ዲህ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥን አት​ጠጪ፥ ርኩስ ነገ​ር​ንም አት​ብዪ፤ ልጁ ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ እስ​ኪ​ሞት ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና አለኝ” ብላ ተና​ገ​ረች። ማኑ​ሄም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወደ እኛ የላ​ክ​ኸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው፥ እባ​ክህ እን​ደ​ገና ወደ እኛ ይምጣ፤ ለሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ልጅ ምን እን​ደ​ም​ና​ደ​ርግ ያስ​ገ​ን​ዝ​በን” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የማ​ኑ​ሄን ቃል ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ እንደ ገና በእ​ርሻ ውስጥ ተቀ​ምጣ ሳለች ወደ ሴቲቱ መጣ፤ ባልዋ ማኑሄ ግን ከእ​ር​ስዋ ጋር አል​ነ​በ​ረም። ሴቲ​ቱም ፈጥና ሮጠች ለባ​ል​ዋም፥ “እነሆ፥ አስ​ቀ​ድሞ ወደ እኔ የመ​ጣው ያ ሰው ደግሞ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ” ብላ ነገ​ረ​ችው። ማኑ​ሄም ተነ​ሥቶ ሚስ​ቱን ተከ​ተለ፤ ወደ ሰው​ዬ​ዉም መጥቶ፥ “ከሚ​ስቴ ጋር የተ​ነ​ጋ​ገ​ርህ አንተ ነህን?” አለው። መል​አ​ኩም፥ “እኔ ነኝ” አለ። ማኑ​ሄም፥ “እነሆ፥ ቃልህ በደ​ረሰ ጊዜ የልጁ ነገሩ፥ ግብ​ሩስ ምን​ድን ነው?” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ማኑ​ሄን፥ “ለሚ​ስ​ትህ ከነ​ገ​ር​ኋት ሁሉ ተጠ​በቁ። ከወ​ይ​ንም ከሚ​ወ​ጣው ሁሉ አት​ብላ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥ​ንም አት​ጠጣ፤ ርኩ​ስ​ንም ነገር ሁሉ አት​ብላ፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ትን ሁሉ ጠብቁ” አለው። ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “የፍ​የል ጠቦት እና​ዘ​ጋ​ጅ​ልህ ዘንድ ግድ እን​ል​ሃ​ለን” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ማኑ​ሄን፥ “አንተ የግድ ብት​ለኝ እህ​ል​ህን አል​በ​ላም፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ብታ​ደ​ርግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ር​በው” አለው። ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መሆ​ኑን አላ​ወ​ቀም ነበር። ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “ነገ​ርህ በደ​ረሰ ጊዜ እን​ድ​ና​ከ​ብ​ርህ ስምህ ማን ነው” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ?” አለው። ማኑ​ሄም የፍ​የ​ሉን ጠቦ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ወስዶ በድ​ን​ጋይ ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​በው። መል​አ​ኩም ተአ​ም​ራት አደ​ረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ይመ​ለ​ከቱ ነበር። ነበ​ል​ባ​ሉም ከመ​ሠ​ዊ​ያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ ነበ​ል​ባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑ​ሄና ሚስ​ቱም ተመ​ለ​ከቱ፤ በም​ድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ዳግ​መኛ ለማ​ኑ​ሄና ለሚ​ስቱ አል​ተ​ገ​ለ​ጠም፤ ያን ጊዜም ማኑሄ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መሆ​ኑን ዐወቀ። ማኑ​ሄም ሚስ​ቱን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ተ​ና​ልና ሞትን እን​ሞ​ታ​ለን” አላት። ሚስ​ቱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ሊገ​ድ​ለን ቢወ​ድድ ኖሮ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ከእ​ጃ​ችን ባል​ተ​ቀ​በ​ለን፥ ይህ​ንም ነገር ሁሉ ባላ​ሳ​የን፥ እን​ዲህ ያለ ነገ​ርም በዚህ ጊዜ ባላ​ሰ​ማን ነበር” አለ​ችው። ሴቲ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሶም​ሶን ብላ ጠራ​ችው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው፤ ልጁም አደገ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሶ​ራ​ሕና በእ​ስ​ታ​ሔል መካ​ከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ጀመረ።

መሳፍንት 13:1-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት እንዲገዙ አሳልፎ ሰጣቸው። ማኑሄ የተባለ ከዳን ወገን የተወለደ አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፤ ሚስቱ መካን ስለ ነበረች ልጅ አልወለደችም። የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። እንግዲህ ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገርም አትብዪ፤ ምክንያቱም ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ልጁ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለአምላክ የተለየ ይሆናልና፤ እስራኤልንም ከፍልስጥኤማውያን እጅ መታደግ ይጀምራል።” ከዚያም ሴቲቱ ወደ ባሏ ሄዳ እንዲህ አለችው፤ “የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ የሚመስልና እጅግ የሚያስደነግጥ ነበር። ከየት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤ ነገር ግን፣ ‘ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገር አትብዪ፤ ልጁም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና’ ብሎኛል።” ከዚያም ማኑሄ፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚወለደውን ልጅ እንዴት አድርገን ማሳደግ አንዳለብን እንዲያስተምረን ያ ወደ እኛ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደ ገና እንዲመጣ ታደርግ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ሴቲቱ በዕርሻ ውስጥ ሳለች ተገለጠላት፤ በዚህ ጊዜ ግን ባሏ ማኑሄ ዐብሯት አልነበረም። እርሷም ለባሏ ለመንገር ፈጥና በመሄድ፣ “ባለፈው ጊዜ የተገለጠልኝ ሰው ዛሬም ተገለጠልኝ” አለችው። ማኑሄም ተነሥቶ ሚስቱን ተከተላት፤ ሰውየው እንደ ደረሰም፣ “ከሚስቴ ጋራ ተነጋግረህ የነበርኸው አንተ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፤ “አዎን እኔ ነኝ” አለው። ማኑሄም፣ “ያልኸው በሚፈጸምበት ጊዜ የልጁ ሕይወት የሚመራው እንዴት ነው? እኛስ ምን ማድረግ አለብን?” ሲል ጠየቀው። የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን እንዲህ አለው፤ “ሚስትህ የነገርኋትን ሁሉ ታድርግ። ከወይን ተክል የሚገኝ ማንኛውንም ነገር አትብላ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤ ርኩስ ነገር አትብላ፤ ያዘዝኋትንም ሁሉ ታድርግ።” ከዚያም ማኑሄ የእግዚአብሔርን መልአክ፣ “የፍየል ጠቦት ዐርደን እስክናዘጋጅልህ ድረስ እባክህ ቈይ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፣ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። ማኑሄ የእግዚአብሔርን መልአክ፣ “የተናገርኸው ሲፈጸም እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” በማለት ጠየቀው። የእግዚአብሔርም መልአክ፣ “ስሜ ድንቅ ስለ ሆነ፣ ለምን ትጠይቀኛለህ?” አለው። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቍርባኑ ጋራ ወስዶ በዐለት ላይ ለእግዚአብሔር ሠዋው። ማኑሄና ሚስቱ እያዩ እግዚአብሔር አስደናቂ ነገር አደረገ፤ ይኸውም የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ዐረገ። ማኑሄና ሚስቱ ይህን ሲመለከቱ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ። የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ዳግመኛ ባለመገለጡ፣ ቀደም ሲል የተገለጠላቸው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ማኑሄ ዐወቀ። ማኑሄም ሚስቱን፣ “እግዚአብሔርን ስላየን ያለ ጥርጥር እንሞታለን” አላት። ሚስቱ ግን መልሳ እንዲህ አለችው፣ “እግዚአብሔር ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቍርባኑን ከእጃችን ባልተቀበለን፤ ደግሞም ይህን ነገር ሁሉ ባላሳየንና እንዲህ ያለውንም ነገር በዚህ ጊዜ ባልነገረን ነበር።” ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሳምሶን ብላ ጠራችው። ልጁ አደገ፤ እግዚአብሔርም ባረከው፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ሳለ ያነቃቃው ጀመር።

መሳፍንት 13:1-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፥ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው። ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፥ ሚስቱም መካን ነበረች፥ ልጅም አልወለደችም። የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፦ እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፥ ልጅም አልወለድሽም፥ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። አሁንም ተጠንቀቂ፥ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ። እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፥ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል። ሴቲቱም ወደ ባልዋ መጥታ፦ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፥ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፥ ከወዴትም እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም። እርሱም፦ እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አሁን የወይን ጠጅ የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ አለኝ ብላ ተናገረች። ማኑሄም፦ ጌታ ሆይ፥ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው፥ እባክህ፥ እንደ ገና ወደ እኛ ይምጣ፥ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንድናደርግ ያስገንዝበን ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፥ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና ለሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች ተገለጠላት፥ ባልዋ ማኑሄ ግን ከእርስዋ ጋር አልነበረም። ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች ለባልዋም፦ እነሆ፥ በቀደም ዕለት ወደ እኔ የመጣው ሰው ደግሞ ተገለጠልኝ ብላ ነገረችው። ማኑሄም ተነሥቶ ሚስቱን ተከተለ፥ ወደ ሰውዮውም መጥቶ፦ ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? አለው። እርሱም፦ እኔ ነኝ አለ። ማኑሄም፦ ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድር ነው? የምናደርግለትስ ምንድር ነው? አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፦ ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ። ከወይንም ከሚወጣው ሁሉ አትብላ፥ የወይን ጠጅንም የሚያሰክርንም ነገር አትጠጣ፥ ርኩስም ነገር ሁሉ አትብላ፥ ያዘዝኋትን ሁሉ ትጠብቅ አለው። ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ፦ የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፥ እባክህ፥ ቆይ አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፦ አንተ የግድ ብትለኝ መብልህን አልበላም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው አለው። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ፦ ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው? አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ፦ ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ? አለው። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቁርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም ተአምራት አደረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም ይመለከቱ ነበር። ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፥ በምድርም በግምባራቸው ተደፉ። የእግዚአብሔርም መልአክ ዳግመኛ ላማኑሄና ለሚስቱ አልተገለጠም፥ ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ማኑሄም ሚስቱን፦ እግዚአብሔርን አይተናልና ሞት እንሞታለን አላት። ሚስቱም፦ እግዚአብሔርስ ሊገድለን ቢወድድ ኖሮ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ከእጃችን ባልተቀበለን፥ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን፥ እንዲህ ያለ ነገርም በዚህ ጊዜ ባላስታወቀን ነበር አለችው። ሴቲቱም ወንድ ልጅ ወለደች፥ ስሙንም ሶምሶን ብላ ጠራችው፥ ልጁም አደገ እግዚአብሔርም ባረከው። የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ።

መሳፍንት 13:1-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የእስራኤል ሕዝብ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ ስለዚህም አርባ ዓመት ሙሉ እንዲገዙአቸው እግዚአብሔር ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ሰጣቸው። በዚያን ዘመን ጾርዓ በምትባል ከተማ የሚኖር ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከዳን ነገድ ነበር፤ ሚስቱ መኻን ስለ ነበረች ልጆች አልወለደችም፤ ለእርስዋም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “አንቺ መኻን ነሽ፤ ልጆችም የሉሽም፤ ነገር ግን ትፀንሺአለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ ከመጠጣትና ማንኛውንም ርኩስ ምግብ ከመብላት ተጠንቀቂ። በእርግጥ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን የራስ ጠጒሩን ፈጽሞ አይላጭ፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።” ከዚህ በኋላ ሴቲቱ መጥታ ለባልዋ እንዲህ አለችው፤ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጥቶ ነበር፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤ እኔ ከወዴት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤ ነገር ግን እርሱ ‘እነሆ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ’ ብሎ ነገረኝ፤ እንዲሁም የሚወለደው ልጅ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በናዝራዊነት ለእግዚአብሔር የተለየ ስለሚሆን፥ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ ከመጠጣትና ማንኛውንም ርኩስ ምግብ ከመብላት እንድጠነቀቅ ነግሮኛል።” ከዚህ በኋላ ማኑሄ “እግዚአብሔር ሆይ! ሕፃኑ ሲወለድ ምን ማድረግ እንደሚገባን ይነግረን ዘንድ ያ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና ተመልሶ ወደ እኛ እንዲመጣ አድርግልን” ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደገና ወጥቶ ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ እንደ ተቀመጠች ተገለጠላት፤ ባልዋ ማኑሄ ከእርስዋ ጋር አልነበረም፤ ስለዚህ በፍጥነት ወደ እርሱ ሮጣ በመሄድ “እነሆ! ያ ከዚህ በፊት ወደ እኔ መጥቶ የነበረው ሰው ዛሬም እንደገና ተገለጠልኝ” አለችው። ማኑሄም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሚስቱን ተከትሎ ሄደ፤ ወደ ሰውየውም ቀርቦ “ከሚስቴ ጋር ተነጋግረህ የነበርከው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም “አዎ! እኔ ነኝ” ሲል መለሰ። ቀጥሎም ማኑሄ “የተናገርከው ቃል ሲፈጸም ለሚወለደው ልጅ ምን መደረግ አለበት?” ሲል ጠየቀው። መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰ፥ “ሚስትህ የነገርኳትን ሁሉ ነገር ለማድረግ ትኲረት መስጠት አለባት። ከወይን ተክል የሚገኝ ምንም ነገር መመገብ አይኖርባትም፤ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤ ማንኛውንም ርኩስ ምግብ አትበላም፤ በአጠቃላይ እኔ ያዘዝኳትን ሁሉ መፈጸም አለባት።” ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ “አንድ የፍየል ጠቦት ዐርደን እስክናዘጋጅልህ ድረስ እባክህ ቈይልን!” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን “ምንም አንተ ብታቈየኝ ምግብህን አልበላም፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትፈልግ ግን ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። ማኑሄም “የተናገርከው ቃል ሲፈጸም ምስጋና እናቀርብልህ ዘንድ ስምህ ማን ነው?” አለው። መልአኩም “ስሜን ለማወቅ የፈለግኸው ለምንድን ነው? ስሜ ድንቅ ነው” ሲል መለሰለት። ከዚህ በኋላ ማኑሄ አንድ የፍየል ጠቦትና የእህል ቊርባን ወስዶ በአለቱ መሠዊያ ላይ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ ማኑሄና ሚስቱም እየተመለከቱ ሳለ እግዚአብሔር አስደናቂ ነገር አደረገ። ነበልባሉ ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ ማኑሄና ሚስቱ እየተመለከቱ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ሆኖ ወደ ላይ ወጣ፤ እነርሱም በግንባራቸው በመሬት ላይ ተደፉ። የእግዚአብሔር መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ዳግመኛ አልተገለጠም ከዚያ በኋላ ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ዐወቀ። ማኑሄ ሚስቱን “እግዚአብሔርን ስላየን በእርግጥ እንሞታለን!” አላት። ሚስቱ ግን “እግዚአብሔር ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ የሚቃጠል መሥዋዕታችንንና የእህል ቊርባናችንን ባልተቀበለም ነበር፤ ይህን ሁሉ አሁን ባላሳየንና እንዲህ ያለውን ነገር ሁሉ ባልነገረንም ነበር” ስትል መለሰችለት። ሴቲቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሶምሶን ብላ ጠራችው፤ ልጁም አደገ፤ እግዚአብሔርም ባረከው፤ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ በነበረበት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ያበረታው ጀመር።

መሳፍንት 13:1-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ስለዚህም ጌታ በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት እንዲገዙ አሳልፎ ሰጣቸው። ማኑሄ የተባለ ከዳን ወገን የተወለደ አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፤ ሚስተ መካን ስለ ነበረች ልጅ አልወለደችም። የጌታም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። እንግዲህ ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገርም አትብይ፤ ምክንያቱም ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ልጁ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና፤ እስራኤልንም ከፍልስጥኤማውያን እጅ መታደግ ይጀምራል።” ከዚያም ሴቲቱ ወደ ባሏ ሄዳ እንዲህ አለችው፤ “የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ የሚመስልና እጅግ የሚያስደነግጥ ነበር። ከየት እንደመጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤ ነገር ግን፥ ‘ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገር አትብይ፤ ልጁም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና’ ብሎኛል።” ከዚያም ማኑሄ፥ “ጌታ ሆይ፥ የሚወለደውን ልጅ እንዴት አድርገን ማሳደግ አንዳለብን እንዲያስተምረን ያ ወደኛ የላከው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና እንዲመጣ እለምንሃለሁ” ብሎ ወደ ጌታ ጸለየ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ሴቲቱ በዕርሻ ውስጥ ሳለች ተገለጠላት፤ በዚህ ጊዜ ግን ባሏ ማኑሄ አብሮአት አልነበረም። እርሷም ለባሏ ለመንገር ፈጥና በመሄድ፥ “ባለፈው ጊዜ የተገለጠልኝ ሰው ዛሬም ተገለጠልኝ” አለችው። ማኑሄም ተነሥቶ ሚስቱን ተከተላት፤ ሰውየው እንደደረሰም፥ “ከሚስቴ ጋር ተነጋግረህ የነበርኸው አንተ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፤ “አዎን እኔ ነኝ” አለው። ማኑሄም፥ “ያልከው በሚፈጸምበት ጊዜ የልጁ ሕይወት የሚመራው እንዴት ነው? እኛስ ምን ማድረግ አለብን?” ሲል ጠየቀው። የጌታም መልአክ እንዲህ አለው፤ “ሚስትህ የነገርኋትን ሁሉ ታድርግ። ከወይን ተክል የሚገኝ ማንኛውንም ነገር አትብላ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤ ርኩስ ነገር አትብላ፤ እኔ ያዘዝኳትን ሁሉ ታድርግ።” ከዚያም ማኑሄ የጌታን መልአክ “የፍየል ጠቦት ዐርደን እስክናዘጋጅልህ ድረስ እባክህ ቈይ” አለው። የጌታም መልአክ፥ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለጌታ አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የጌታ መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። ማኑሄ የጌታን መልአክ፥ “የተናገርከው ሲፈጸም እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” በማለት ጠየቀው። የጌታም መልአክ፥ “ስሜ ድንቅ ስለ ሆነ፥ ለምን ትጠይቀኛለህ?” አለው። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቁርባኑ ጋር ወስዶ በዐለት ላይ ለጌታ ሠዋው። ማኑሄና ሚስቱ እያዩ ጌታ አስደናቂ ነገር አደረገ፤ የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ፥ የጌታ መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ዐረገ። ማኑሄና ሚስቱ ይህን ሲመለከቱ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ። የጌታም መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ዳግመኛ ባለመገለጡ፥ ቀደም ሲል የተገለጠላቸው የጌታ መልአክ መሆኑን ማኑሄ ዐወቀ። ሚስቱንም፥ “እግዚአብሔርን ስላየን ያለ ጥርጥር እንሞታለን” አላት። ሚስቱ ግን መልሳ እንዲህ አለችው፥ “ጌታ ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፥ የሚቃጠለውን መሥዋትና የእህል ቁርባኑን ከእጃችን ባልተቀበለን፤ ደግሞም ይህን ነገር ሁሉ ባላሳየንና እንዲህ ያለውንም ነገር በዚህ ጊዜ ባልነገረን ነበር።” ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሳምሶን ብላ ጠራችው፤ ልጁ አደገ፤ ጌታም ባረከው፤ የጌታም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ሳለ ያነቃቃው ጀመር።