መሳፍንት 10:1-5
መሳፍንት 10:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከአቤሜሌክም በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የአባቱ ወንድም ልጅ የፎሓ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም በኤፍሬም ተራራ በሳምር ተቀምጦ ነበር። እስራኤልንም ሃያ ሦስት ዓመት ገዛ፤ ሞተም፤ በሳምርም ተቀበረ። ከእርሱም በኋላ ገለዓዳዊዉ ኢያዕር ተነሣ፤ እስራኤልንም ሃያ ሁለት ዓመት ገዛ። በሠላሳ ሁለት የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ሁለት ልጆችም ነበሩት፤ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተሞች ነበሩአቸው። ኢያዕርም ሞተ፤ በራሞንም ተቀበረ።
መሳፍንት 10:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከአቢሜሌክ በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የዱዲ ልጅ፣ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ሳምር በምትባል መንደር ይኖር ነበር። ቶላ በእስራኤል ላይ ሃያ ሦስት ዓመት በፈራጅነት ከተቀመጠ በኋላ ሞተ፤ በሳምርም ተቀበረ። ከቶላ ቀጥሎ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፤ እርሱም በእስራኤል ላይ ሃያ ሁለት ዓመት በፈራጅነት ተቀመጠ። ኢያዕር በሠላሳ አህዮች የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ልጆቹም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች በገለዓድ ምድር ነበሯቸው። ኢያዕር ሞተ፤ በቃሞንም ተቀበረ።
መሳፍንት 10:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከአቤሜሌክም በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የዱዲ ልጅ የፎሓ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፥ በተራራማውም በኤፍሬም አገር ባለችው በሳምር ተቀምጦ ነበር። በእስራኤልም ላይ ሀያ ሦስት ዓመት ፈረደ፥ ሞተም፥ በሳምርም ተቀበረ። ከእርሱም በኋላ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፥ በእስራኤልም ላይ ሀያ ሁለት ዓመት ፈረደ። በሠላሳ የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ልጆችም ነበሩት፥ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው። ኢያዕርም ሞተ፥ በቃሞንም ተቀበረ።
መሳፍንት 10:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አቤሜሌክ ከሞተ በኋላ የዶዶ የልጅ ልጅ የፑአ ልጅ ቶላዕ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም ከይሳኮር ነገድ ሲሆን የሚኖረውም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ሻሚር ተብላ በምትጠራ ስፍራ ነበር፤ ይህ ሰው ኻያ ሦስት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆኖ ከቆየ በኋላ ሞተ፤ በሻሚርም ተቀበረ። ከቶላዕ ቀጥሎ ገለዓዳዊው ያኢር ተነሣ፤ እርሱም ኻያ ሁለት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆነ፤ በሠላሳ አህዮች ላይ ተቀምጠው የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በገለዓድ ምድር ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው፤ እነዚህም ከተሞች እስከ ዛሬ የያኢር መንደሮች ተብለው ይጠራሉ፤ ያኢር ሞተ፤ በቃሞንም ተቀበረ።
መሳፍንት 10:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከአቤሜሌክ በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የዱዲ ልጅ፥ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ሳምር በምትባል መንደር ይኖር ነበር። ቶላ በእስራኤል ላይ ሃያ ሦስት ዓመት በፈራጅነት ከተቀመጠ በኋላ ሞተ፤ በሳምርም ተቀበረ። ከቶላ ቀጥሎ ገለዓዳዊው ያኢር ተነሣ፤ እርሱም በእስራኤል ላይ ሃያ ሁለት ዓመት በፈራጅነት ተቀመጠ። ያኢር በሠላሳ አህዮች የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ልጆቹም እስከ ዛሬ ድረስ የያኢር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች በገለዓድ ምድር ነበሯቸው። ያኢር ሞተ፤ በቃሞንም ተቀበረ።