ያዕቆብ 4:13-15
ያዕቆብ 4:13-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አሁንም “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን፤ በዚያም ዓመት እንኖራለን፤ እንነግድማለን፤ እናተርፍማለን፤” የምትሉ እናንተ! ተመልከቱ፤ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። በዚህ ፈንታ “ጌታ ቢፈቅድ፥ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን፤” ማለት ይገባችኋል።
ያጋሩ
ያዕቆብ 4 ያንብቡያዕቆብ 4:13-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እናንተ፣ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ወይም ወደዚያች ከተማ እንሄዳለን፤ በርሷም አንድ ዓመት እንቈያለን፤ እንነግዳለን፤ እናተርፋለንም” የምትሉ እንግዲህ ስሙ። ነገ የሚሆነውን እንኳ አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድን ናት? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁ። ይልቁንም፣ “የጌታ ፈቃድ ቢሆን እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል።
ያጋሩ
ያዕቆብ 4 ያንብቡያዕቆብ 4:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። በዚህ ፈንታ፦ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።
ያጋሩ
ያዕቆብ 4 ያንብቡ