ኢሳይያስ 66:18-19 - Compare All Versions

ኢሳይያስ 66:18-19 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“ሥራ​ቸ​ው​ንና አሳ​ባ​ቸ​ውን ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ እነ​ሆም እኔ እመ​ጣ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንና ልሳ​ና​ት​ንም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ፤ ክብ​ሬ​ንም ያያሉ። በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ምል​ክት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከሞት የዳ​ኑ​ትን ዝና​ዬን ወዳ​ል​ሰሙ፥ ክብ​ሬ​ንም ወዳ​ላዩ ወደ አሕ​ዛብ ወደ ተር​ሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ኤላድ በሩቅ ወዳሉ ደሴ​ቶች እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ክብ​ሬን ይና​ገ​ራሉ።

ኢሳይያስ 66:18-19 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“እኔም ሥራቸውንና ሐሳባቸውን ስለማውቅ፣ መንግሥታትንና ልሳናትን ሁሉ ልሰበስብ እመጣለሁ፤ እነርሱም መጥተው ክብሬንም ያያሉ። “በመካከላቸው ምልክት አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም የተረፉትን አንዳንዶቹን ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፣ ወደ ፉጥ፣ ወደ ታወቁት ቀስተኞች ወደ ሉድ፣ ወደ ቶቤልና ያዋን እንዲሁም ዝናዬን ወዳልሰሙትና ክብሬን ወዳላዩት ራቅ ወዳሉት ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በሕዝቦችም መካከል ክብሬን ይናገራሉ።

ኢሳይያስ 66:18-19 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቄአለሁና፥ አሕዛብንና ልሳትን ሁሉ የምሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል፥ እነርሱም ይመጣሉ ክብሬንም ያያሉ። በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ ወደ ፉጥ ወደ ሉድ ወደ ሞሳሕ ወደ ቶቤል ወደ ያዋን በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፥ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።

ኢሳይያስ 66:18-19 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እኔ ሥራቸውንና ሐሳባቸውን ስለማውቅ የተለያየ ቋንቋ ያላቸውን ሕዝቦች ሁሉ እሰበስባለሁ፤ መጥተውም የእኔን ክብር ያያሉ። በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከሞት ከተረፉት መካከል ስለ እኔ ወዳልሰሙትና ክብሬንም ወዳላዩት ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ወደ ተርሴስ፥ ወደ ሊብያውያን ቀስት ወደሚያስፈነጥሩ ወደ ሊድያውያን፥ ወደ ቱባል፥ ወደ ግሪክ፥ ራቅ ብለው ወደሚገኙት ደሴቶችም እልካቸዋለሁ፤ እነርሱም በሕዝቦች መካከል ክብሬን ይገልጣሉ።

ኢሳይያስ 66:18-19 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቃለሁ፤ አሕዛብንና ልሣናትን ሁሉ የምትሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል፤ እነርሱም ይመጣሉ፥ ክብሬንም ያያሉ። በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።