ኢሳይያስ 65:2-3
ኢሳይያስ 65:2-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በጽድቅ መንገድ ወደማይሄዱ፥ ኀጢአታቸውን ወደሚከተሉ ዐመፀኞች ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆችን ዘረጋሁ። እኒህ ሕዝብ ዘወትር የሚያስቈጡኝ ናቸው፤ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ በጡብም ላይ ለአጋንንት የሚያጥኑ፥
ኢሳይያስ 65:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ለዐመፀኛ ሕዝብ፣ መልካም ባልሆኑ መንገዶች ለሚሄዱ፣ የልባቸውን ምኞት ለሚከተሉ፣ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ። ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝቦች፣ በአትክልት ቦታዎች መሥዋዕት የሚያቀርቡ፣ በሸክላ መሠዊያዎች ላይ ዕጣን የሚያጥኑ፣ ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝብ ናቸው፤
ኢሳይያስ 65:2-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
መልካም ባልሆነው መንገድ፥ አሳባቸውን እየተከተሉ፥ ወደሚሄዱ ወደ ዓመፀኛ ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆቼን ዘረጋሁ። ይህ ሕዝብ ዘወትር የሚያስቈጡኝ ናቸው፥ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ በጡብም ላይ የምያጥኑ፥