ኢሳይያስ 63:7
ኢሳይያስ 63:7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በስጦታው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና ዐሰብሁ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ወገኖች እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸርነቱና እንደ ጽድቁ ብዛትም ይቅርታውን ያመጣልናል።
ኢሳይያስ 63:7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ እግዚአብሔር ስላደረገልን ሁሉ፣ ስለሚመሰገንበት ሥራው፣ እንደ ፍቅሩና እንደ ቸርነቱ መጠን፣ ለእስራኤል ቤት ያደረገውን፣ አዎን፣ ስላደረገው መልካም ነገር እናገራለሁ።
ኢሳይያስ 63:7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ።