ኢሳይያስ 58:3-7

ኢሳይያስ 58:3-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ስለ ምን ጾምን፥ አን​ተም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ኸ​ንም? ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንስ ስለ ምን አዋ​ረ​ድን፥ አን​ተም አላ​ወ​ቅ​ኸ​ንም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾ​ማ​ችሁ ቀን ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፥ ሠራ​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ታስ​ጨ​ን​ቃ​ላ​ችሁ። እነሆ፥ ለጠ​ብና ለክ​ር​ክር ትጾ​ማ​ላ​ችሁ፤ ድሃ​ው​ንም በጡጫ ትማ​ታ​ላ​ችሁ፤ በም​ት​ጮ​ኹ​በት ጊዜ ድም​ፃ​ችሁ እን​ዲ​ሰማ ለእኔ ትጾ​ማ​ላ​ች​ሁን? ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እን​ደ​ም​ት​ጾ​ሙት አት​ጾ​ሙም። እኔ ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እን​ደ​ዚ​ችም ባለች ቀን ሰው ራሱን ቢያ​ሳ​ዝን፥ አን​ገ​ቱ​ንም እንደ ቀለ​በት ቢያ​ቀ​ጥን፥ ማቅ ለብሶ በአ​መድ ላይ ቢተ​ኛም፥ ይህ ጾም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም። ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን የበ​ደ​ልን እስ​ራት ፍታ፤ ጠማ​ማ​ውን ሁሉ አቅና፤ የተ​ጨ​ነ​ቀ​ው​ንም ሁሉ አድን፤ የዐ​መፃ ደብ​ዳ​ቤ​ንም ተው። ለተ​ራ​በ​ውም እን​ጀ​ራ​ህን አጥ​ግ​በው፤ ድሆ​ችን ወደ ቤትህ አስ​ገ​ብ​ተህ አሳ​ድ​ራ​ቸው፤ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ብታይ አል​ብ​ሰው፤ ከሥጋ ዘመ​ድህ አት​ሸ​ሽግ።

ኢሳይያስ 58:3-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

‘አንተ ካልተቀበልኸው፣ ስለ ምን ብለን ጾምን? አንተ ከጕዳይ ካልቈጠርኸው፣ ስለ ምን ራሳችንን አዋረድን?’ ይላሉ። “ሆኖም በጾማችሁ ቀን የልባችሁን ታደርጋላችሁ፤ ሠራተኞቻችሁንም ትበዘብዛላችሁ። ጾማችሁ በጥልና በክርክር፣ በግፍ ጡጫና በመደባደብ ይፈጸማል፤ ከእንግዲህ ዛሬ እንደምትጾሙት ጾማችሁ፣ ድምፃችሁ ወደ ላይ እንደሚሰማ ተስፋ አታድርጉ። እኔ የመረጥሁት ጾም እንዲህ ዐይነቱን ነውን? ሰውስ ራሱን የሚያዋርደው በእንዲህ ያለው ቀን ብቻ ነውን? እንደ ደንገል ራስን ዝቅ ማድረግ ነውን? ወይስ ማቅ ለብሶ በዐመድ ላይ መንከባለል ነውን? ታዲያ ጾም ብለህ የምትጠራው ይህን ነውን? እግዚአብሔርስ የሚቀበለው እንዲህ ያለውን ቀን ነውን? “እንግዲህ እኔ የመረጥሁት ጾም፣ የጭቈናን ሰንሰለት እንድትበጥሱ፣ የቀንበርን ገመድ እንድትፈቱ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንድታወጡ፣ ቀንበርን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን? ምግብህን ለተራበ እንድታካፍለው፣ ተንከራታቹን ድኻ ወደ ቤትህ እንድታስገባው፣ የተራቈተውን ስታይ እንድታለብሰው፣ የሥጋ ዘመድህንም ፊት እንዳትነሣው አይደለምን?

ኢሳይያስ 58:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ። እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፥ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም። እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለሁ? እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለንም? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?

ኢሳይያስ 58:3-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሕዝቡም “እነሆ እኛ እንጾማለን፤ አንተ ግን አትመለከተንም፤ የማትመለከተንስ ከሆነ ሰውነታችንን ለምን እናዋርዳለን?” ይላሉ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “እነሆ እናንተ በምትጾሙበት ጊዜ የልባችሁን ፈቃድ ትፈጽማላችሁ፤ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ትጨቊናላችሁ፤ የጾማችሁ መጨረሻው ጠብና ጭቅጭቅ ስለ ሆነ ጭካኔ በተሞላበት ቡጢ ትማታላችሁ፤ እንደዚህ አድርጋችሁ የምትጾሙት ጾም ጸሎታችሁን በላይ በሰማይ እንዲሰማ አያደርገውም። እናንተ በምትጾሙበት ጊዜ ሰውነታችሁን ታጐሳቊላላችሁ፤ ራሳችሁን እንደ ሸምበቆ ዝቅ ታደርጋላችሁ፤ አመድ ነስንሳችሁ፥ ማቅም አንጥፋችሁ ትተኛላችሁ? ታዲያ እናንተ ጾም የምትሉት ይህን ነውን? እኔስ በዚህ ዐይነቱ ጾም ደስ የሚለኝ ይመስላችኋልን? “እኔ የምደሰትበት ጾም የጭቈና ሰንሰለትና የፍትሕ መጓደል ቀንበር ታላሉ ዘንድ፥ ቀንበሩን ሰብራችሁ የተጨቈኑትን ነጻ ታወጡ ዘንድ አይደለምን? ምግባችሁን ከተራበ ሰው ጋር እንድትካፈሉ፥ ማደሪያ የሌለውን ድኻ በቤታችሁ እንድትቀበሉ፥ የተራቈቱትን እንድታለብሱ፥ ከቅርብ ዘመዶቻችሁም ራሳችሁን እንዳትደብቁ አይደለምን?

ኢሳይያስ 58:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ስለምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ። እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ፤ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ለማሰማት ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም። እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነው? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነው? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ እንዲያደርግ፥ ማቅንና አመድንም በበታቹ እንዲያነጥፍ ነው? በውኑ ይህን ጾም፥ በጌታ ዘንድ የተወደደ ቀን ብለህ ትጠራዋለህ? እኔስ የመረጥሁት ጾም፥ የበደልን እስራት እንድትፈቱ፥ የቀንበርንስ ጠፍር እንድትለቁ፥ የተገፉትን አርነት እንድታወጡ፥ ቀንበሩን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?