ኢሳይያስ 44:24-28

ኢሳይያስ 44:24-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከማ​ኅ​ፀን የሠ​ራህ፥ የሚ​ቤ​ዥህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሁሉን ለብ​ቻዬ የፈ​ጠ​ርሁ፥ ሰማ​ያ​ትን የዘ​ረ​ጋሁ፥ ምድ​ር​ንም ያጸ​ናሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ በሟ​ርት ሙት እና​ስ​ነ​ሣ​ለን የሚ​ሉ​ትን፥ ከል​ባ​ቸ​ውም አን​ቅ​ተው ሐሰት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሰዎች ምል​ክት የሚ​ለ​ውጥ ማን ነው? ጥበ​በ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ኋላ ይመ​ል​ሳል፤ ምክ​ራ​ቸ​ው​ንም ስን​ፍና ያደ​ር​ጋል። የባ​ር​ያ​ውን ቃል ያጸ​ናል፤ የመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ምክር ይፈ​ጽ​ማል። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ኛ​ለሽ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ትታ​ነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ምድረ በዳ​ዎ​ች​ዋም ይለ​መ​ል​ማሉ፤” ይላል፤ ቀላ​ይ​ዋ​ንም፥ “ደረቅ ሁኚ ፈሳ​ሾ​ች​ሽም ይድ​ረቁ” ይላል፤ ቂሮ​ስ​ንም፥ “ብልህ ሁን፤ እር​ሱም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም እመ​ሠ​ር​ታ​ለሁ ብሎ ፈቃ​ዴን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል” ይላል።