ኢሳይያስ 44:16 - Compare All Versions
ኢሳይያስ 44:16 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፤ በዚያም በግማሹ ሥጋ ይጠብሳል፤ ጥብሱንም ይበላና ይጠግባል፤ ይሞቃልና፥ “እሰይ ሞቅሁ፥ እሳቱን አይቻለሁ” ይላል።
ኢሳይያስ 44:16 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ግማሹን ዕንጨት ያነድደዋል፤ በላዩ ምግቡን ያበስልበታል፤ ሥጋ ጠብሶበት እስኪጠግብ ይበላል፤ እሳቱን እየሞቀ እንዲህ ይላል፤ “ዕሠይ ሞቀኝ፤ እሳቱም ይታየኛል።”
ኢሳይያስ 44:16 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፥ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል፥ ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል፥ ይሞቃልና፦ እሰይ ሞቅሁ፥ እሳቱን አይቻለሁ ይላል።
ኢሳይያስ 44:16 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ግማሹን እሳት አንድዶ ምግቡን ያዘጋጅበታል፤ ሥጋም ጠብሶ እስከሚጠግብ ይመገባል፤ ከሞቀውም በኋላ “ግሩም እሳት ነው! እንዴት ይሞቃል!” ይላል።
ኢሳይያስ 44:16 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፥ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል፤ ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል፤ ይሞቃልና፦ “እሰይ ሞቅሁ፥ ሙቀት ተሰማኝ” ይላል።