ኢሳይያስ 42:17-25

ኢሳይያስ 42:17-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በተ​ቀ​ረ​ጹ​ትም ምስ​ሎች የሚ​ታ​መኑ፥ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፈጽ​መ​ውም ያፍ​ራሉ። እና​ንተ ደን​ቆ​ሮች፥ ስሙ፤ እና​ን​ተም ዕው​ሮች እዩ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም። ከባ​ሪ​ያ​ዎች በቀር ዕውር ማን ነው? ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውስ በቀር ደን​ቆሮ የሆነ ማን ነው? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ታወሩ። ብዙ ነገ​ርን ታያ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን አት​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትም፤ ጆሮ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ተከ​ፍ​ተ​ዋል፤ ነገር ግን አት​ሰ​ሙም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ምስ​ጋ​ና​ውን ያጸ​ድ​ቅና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መከረ። እነሆ፥ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ሕዝቡ የተ​በ​ዘ​በ​ዘና የተ​ዘ​ረፈ ነው፤ ወጥ​መድ በሁ​ሉም ቦታ በዋ​ሻ​ዎ​ችና እነ​ር​ሱን በሸ​ሸ​ጉ​ባ​ቸው ቤቶች ተጠ​ም​ዶ​አል፤ ብዝ​በዛ ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ድ​ንም የለም፤ ምር​ኮም ሆነ​ዋል፤ የሚ​ያ​ስ​ጥ​ላ​ቸ​ውም የለም። ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ምጥ፥ ለሚ​መ​ጣ​ውም ጊዜ የሚ​ሰማ ማን ነው? ያዕ​ቆ​ብን እን​ዲ​ማ​ር​ኩት፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም እን​ዲ​በ​ዘ​ብ​ዙት ያደ​ረገ ማን ነው? እነ​ር​ሱም የበ​ደ​ሉት፥ በመ​ን​ገ​ዱም ይሄዱ ዘንድ ያል​ወ​ደ​ዱት፥ ሕጉ​ንም ያል​ሰ​ሙት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ዚህ የቍ​ጣ​ውን መዓ​ትና የሰ​ል​ፉን ጽናት አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸው አቃ​ጠ​ላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁም፤ በል​ባ​ቸ​ውም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።

ኢሳይያስ 42:17-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም። “እናንተ ደንቈሮዎች ስሙ፤ እናንተ ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም! አገልጋዬ እንጂ፣ ሌላ ዕውር ማን አለ? ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ማን ደንቈሮ አለ? ለእኔ ታማኝ እንደ ሆነ ሰው የታወረ፣ እንደ እግዚአብሔርስ አገልጋይ ዕውር ማነው? ብዙ ነገርን አያችሁ፤ ነገር ግን አላስተዋላችሁም፤ ጆሯችሁ ክፍት ነው፤ ነገር ግን ምንም አትሰሙም።” እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሲል፣ ሕጉን ታላቅና የተከበረ በማድረግ ደስ አለው። ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ፣ በጕድጓድ ውስጥ የተጠመደበት፣ በወህኒ ቤት የተዘጋበት ነው፤ ተበዝብዘዋል፣ የሚያድናቸውም የለም፤ ተማርከዋል፣ “መልሷቸው” የሚልም የለም። ከእናንተ ይህን የሚሰማ፣ ለሚመጣውም ጊዜ አስተውሎ የሚያደምጥ ማነው? ያዕቆብን ለዝርፊያ፣ እስራኤልን ለምርኮ የዳረገ ማነው? በኀጢአት የበደልነው፣ እግዚአብሔር አይደለምን? መንገዱን ለመከተል፣ ለሕጉም መታዘዝ አልፈለጉምና። ስለዚህ የሚነድድ ቍጣውን፣ የጦርነትንም መዓት አፈሰሰባቸው፤ በእሳት ነበልባል ከበባቸው፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን ልብ አላሉም።

ኢሳይያስ 42:17-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፦ አምላኮቻችን ናችሁ የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፈጽመውም ያፍራሉ። እናንተ ደንቆሮች፥ ስሙ፥ እናንተም ዕውሮች፥ ታዩ ዘንድ ተመልከቱ። ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው? ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትጠባበቁትም፥ ጆሮአችሁም ተከፍተዋል፥ ነገር ግን አትሰሙም። እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ። ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፥ ሁላቸው በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፥ ብዝበዛ ሆነዋል የሚያድንም የለም፥ ምርኮም ሆነዋል፥ ማንም፦ መልሱ አይልም። ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፥ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው? ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ይሄዱ ዘንድ ያልወደዱት ለሕጉም ያልታዘዙለት እግዚአብሔር እርሱ አይደለምን? ስለዚህ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰበት፥ በዙሪያም አነደደው እርሱ ግን አላወቀም፥ አቃጠለውም እርሱ ግን ልብ አላከረገም።

ኢሳይያስ 42:17-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በጣዖቶች ተማምነው ምስሎችን ‘እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ ኀፍረት ይደርስባቸዋል።” “እናንተ ደንቆሮዎች አድምጡ! እናንተም ዕውሮች አተኲራችሁ ተመልከቱ! ከአገልጋዬ በቀር ዕውር ማነው? ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ ማነው? ራሱን ለእኔ እንዳስገዛው ያለው ዕውር ማን ነው? ወይም እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ ያለ ዕውር ማን ነው? እስራኤል ሆይ! ብዙ ነገር አይተሃል፤ ነገር ግን ልብ ብለህ አላስተዋልከውም፤ ጆሮዎችህም ክፍት ናቸው፤ ነገር ግን አንተ አትሰማም።” እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርዱን ለማጠናከር ሕጉን ታላቅና የተከበረ ያደርገው ዘንድ ፈቀደ። ሕዝቡ ግን ተዘርፈውና ተበዝብዘው በዋሻ ውስጥ ተዘግቶባቸዋል፤ በወህኒ ቤትም ተሸሽገዋል። ተዘረፉ፤ ተበዘበዙ፤ ማንም በመታደግ ሊያድናቸው አልቻለም። ከእናንተ መካከል ለዚህ ትኲረት ሰጥቶ ስለሚመጣው ጊዜ በጥንቃቄ የሚያዳምጥ ማነው? የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን ለዘራፊና ለቀማኛ አሳልፎ የሰጠ ማነው? ይህን ያደረገው እግዚአብሔር ራሱ አይደለምን? ይህም የሆነው እኛ ስለ በደልነው፥ በሚፈቅደው መንገድ ስላልሄድንና ለሕጉም ታዛዦች ስላልሆንን ነው። ስለዚህ የቊጣውን ግለትና አስፈሪውን ጦርነት በላያችን ላይ አወረደ፤ በዙሪያችን እሳት አቀጣጠለ፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ አልተረዳነውም፤ አቃጠለን ልብም አላደረግነውም።

ኢሳይያስ 42:17-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፦ “አምላኮቻችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፈጽመውም ያፍራሉ። እናንተ ደንቆሮች፥ ስሙ፤ እናንተም ዕውሮች፥ ታዩ ዘንድ ተመልከቱ። ከአገልጋዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹም ተገዢዬ ወይም እንደ ጌታ አገልጋይ ዕውር የሆነ ማን ነው? ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትጠባበቁም፤ ጆሮአችሁም ተከፍተዋል፥ ነገር ግን አትሰሙም። ጌታ ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ። ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁሉም በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል፤ በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ተበዝብዘዋል የሚያድንም የለም፥ ተማርከዋል፤ “መልሷቸው” የሚል ማንም የለም። ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፥ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው? ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ለመሄድ ያልወደዱት፥ ለሕጉም ያልታዘዙለት ጌታ እርሱ አይደለምን? ስለዚህ የቁጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰባቸው፤ በዙሪያቸውም አነደደው፤ እነርሱ ግን አላወቁም፥ አቃጠላቸውም እነርሱ ግን ልብ አላሉም።