ኢሳይያስ 41:9-10
ኢሳይያስ 41:9-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ፥ ከማዕዘንዋም የጠራሁህ ነህና፦ አንተ ባሪያዬ ነህ፤ መርጬሃለሁ፤ አልጥልህም፤ ያልሁህ ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ኢሳይያስ 41:9-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከምድር ዳርቻ ያመጣሁህ፣ ከአጥናፍም የጠራሁህ፣ ‘አንተ ባሪያዬ ነህ’ ያልሁህ፤ መረጥሁህ እንጂ አልጣልሁህም። እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ኢሳይያስ 41:9-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፦ አንተ ባሪያዬ ነህ መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፥ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ኢሳይያስ 41:9-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከምድር ዳርቻ አመጣሁህ፥ ከአራቱም ማእዘን ጠራሁህ፤ ‘አገልጋዬ ትሆናለህ’ ብዬ መረጥኩህ እንጂ አልጣልኩህም። እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።