ኢሳይያስ 41:13 - Compare All Versions

ኢሳይያስ 41:13 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ቀኝ እጅ​ህን የያ​ዝ​ሁህ፥ እን​ዲ​ህም የም​ልህ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና።

ኢሳይያስ 41:13 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና አትፍራ ይልሃል፤ እረዳሃለሁ።

ኢሳይያስ 41:13 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፦ አትፍራ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።

ኢሳይያስ 41:13 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

‘አይዞህ አትፍራ፥ አትደንግጥ፥ ቀኝ እጅህን ይዤ እረዳሃለሁ’ እያልኩ የማበረታታህ፥ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።”

ኢሳይያስ 41:13 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እኔ አምላክህ ጌታ ነኝ፦ “አትፍራ፥ እረዳሃለሁ” ብዬ ቀኝህን የያዝኩ።