ኢሳይያስ 40:7-8 - Compare All Versions

ኢሳይያስ 40:7-8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ት​ን​ፋስ ይነ​ፍ​ስ​በ​ታ​ልና ሣሩ ይደ​ር​ቃል፤ አበ​ባ​ውም ይረ​ግ​ፋል፤ በእ​ው​ነት ሕዝቡ ሣር ነው። ሣሩ ይደ​ር​ቃል፤ አበ​ባ​ውም ይረ​ግ​ፋል፤ የአ​ም​ላ​ካ​ችን ቃል ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንቶ ይኖ​ራል።”

ኢሳይያስ 40:7-8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነፍሶበታልና፤ ሕዝቡ በርግጥ ሣር ነው። ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”

ኢሳይያስ 40:7-8 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው። ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ ያምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

ኢሳይያስ 40:7-8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የእግዚአብሔር ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ፥ ሣሩ እንደሚደርቅና አበባውም እንደሚረግፍ ሰውም እንዲሁ ረጋፊ ነው። በእርግጥ ሣር ይደርቃል፤ አበባም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።”

ኢሳይያስ 40:7-8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

የጌታ እስትንፋስ ይነፍስበታል፤ ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው። ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንታ ትኖራለች።