ኢሳይያስ 39:6 - Compare All Versions
ኢሳይያስ 39:6 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አያስቀሩልህም፤ ይላል እግዚአብሔር።
ኢሳይያስ 39:6 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
እነሆ፤ በቤተ መንግሥትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ድረስ ያከማቹትም ሁሉ ወደ ባቢሎን ተማርኮ የሚወሰድበት ቀን ይመጣል፤ አንዳች የሚተርፍ ነገር የለም፤ ይላል እግዚአብሔር።
ኢሳይያስ 39:6 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እነሆ፥ በቤትህ ያለውን ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፥ ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።
ኢሳይያስ 39:6 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
የቀድሞ አባቶች እስከዚህች ቀን ያከማቹት በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርልህም።
ኢሳይያስ 39:6 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እነሆ፥ በቤትህ ያለውን ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል ጌታ።