ኢሳይያስ 33:14-15
ኢሳይያስ 33:14-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎችን ያዘ፤ እሳት እንደሚነድድ የሚነግራችሁ ማን ነው? የዘለዓለም ሀገርንስ የሚነግራችሁ ማን ነው? በጽድቅ የሚሄድ፥ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በደልንና ኀጢአትን የሚጠላ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚደፍን፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።
ኢሳይያስ 33:14-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ደነገጡ፤ አምላክ የሌላቸውም ፍርሀት ይዟቸው፣ “ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳት ጋራ ማን መኖር ይችላል፣ ከዘላለም እሳትስ ጋራ ማን መኖር ይችላል?” አሉ። በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣
ኢሳይያስ 33:14-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፥ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ፥ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለምም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቍር፥ ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው።
ኢሳይያስ 33:14-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ። በእውነትና በትክክል የሚናገሩ፥ በግፍ የሚገኝን ትርፍ የሚጸየፉ፥ ጉቦን ከመቀበል ይልቅ የሚያስወግዱ፥ ስለ ነፍስ ግድያ መስማት የማይፈልጉና፥ ክፉ ነገርን ከማየት ዐይኖቻቸውን የሚጨፍኑ፥
ኢሳይያስ 33:14-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ አምላክ የሌላቸው በፍርሃት ራዱ፤ “ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ? ለዘለዓለምም ከምትነድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ?” በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በጭቆና የሚገኝ ትርፍን የሚጸየፍ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚሰበስብ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚከልል፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።