ኢሳይያስ 3:8-11
ኢሳይያስ 3:8-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢየሩሳሌም ተፈትታለችና፥ ይሁዳም ወድቃለችና፥ አንደበታቸውም ዐመፅን ስለሚናገር ለእግዚአብሔር አልታዘዙም። ዛሬም ክብራቸው ተዋርዷልና፥ ፊታቸውም አፍሯልና ኀጢአታቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ኀጢአት ተቃወመቻቸው፤ በላያቸውም ተገልጣ ታወቀች። ክፉ ምክርን መክረዋልና ለነፍሳቸው ወዮላት! እንዲህም አሉ፥ “ጻድቁን እንሻረው፤ ሸክም ሆኖብናልና፤” ስለዚህ የእጃቸውን ሥራ ፍሬ ይበላሉ። እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደረግበታልና ለበደለኛ ወዮ! ክፉም ይደርስበታል።
ኢሳይያስ 3:8-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢየሩሳሌም ተንገዳግዳለች፤ ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚቃወም፣ የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና። የፊታቸው ገጽታ ይመሰክርባቸዋል፤ ኀጢአታቸውን እንደ ሰዶም በይፋ ይናገራሉ፤ አይደብቁትምም፤ ጥፋትን በራሳቸው ላይ ስላመጡ፣ ወዮላቸው! ጻድቃን መልካም ነገር እንደሚያገኙ ንገሯቸው፤ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና። በደለኞች ወዮላቸው! ጥፋት ይመጣባቸዋል! የእጃቸውን ያገኛሉና።
ኢሳይያስ 3:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የክብሩን ዓይን ያስቈጡ ዘንድ ምላሳቸውና ሥራቸው በእግዚአብሔር ላይ ነውና ኢየሩሳሌም ተፈታች ይሁዳም ወደቀ። የፊታቸውም እፍረት ይመሰክርባቸዋል፥ እንደ ሰዶምም ኃጢአታቸውን ያወራሉ፥ አይሠውሩአትም። በራሳቸው ላይ ክፉ ነገርን ሠርተዋልና ለነፍሳቸው ወዮ! የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና ጻድቁን፦ መልካም ይሆንልሃል በሉት። እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደረግበታልና ለበደለኛ ወዮ! ክፉም ደርሶበታል።
ኢሳይያስ 3:8-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሩሳሌም ተሰናክላ በመንገዳገድ ላይ ናት፤ ይሁዳም ልትወድቅ ተቃርባለች፤ ምክንያቱም የሚናገሩትም ሆነ የሚሠሩት ሁሉ እግዚአብሔርን በመፈታተን ስለ ሆነ ክብሩን አቃለዋል። ለሚመለከታቸው ሰው ፊታቸው ይመሰክርባቸዋል፤ እንደ ሰዶም ሰዎች ሳይደብቁ ኃጢአታቸውን በግልጽ ይናገራሉ፤ በራሳቸው ላይ ጥፋትን ስላመጡ ወዮላቸው። ሁሉ ነገር ስለሚሳካላቸውና የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ጻድቃንን የተባረካችሁ ናችሁ በሉአቸው። ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!
ኢሳይያስ 3:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ኢየሩሳሌም ተንገዳገዳለች፤ ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው ጌታን የሚቃወም፤ የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና። የፊታቸው ገጽታ ይመሰክርባቸዋል፤ ኀጢአታቸውን እንደ ሰዶም በይፋ ይናገራሉ፤ አይደብቁትምም፤ ጥፋትን በራሳቸው ላይ ስላመጡ ወዮላቸው! ጻድቃን መልካም ነገር እንደሚያገኙ ንገሯቸው፤ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና። የእጃቸውን ያገኛሉና። በደለኞች ወዮላቸው፤ ጥፋት ይመጣባቸዋል፤