ኢሳይያስ 26:9
ኢሳይያስ 26:9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ትእዛዝህ በምድር ላይ ብርሃን ነውና ነፍሴ በሌሊት ወደ አንተ ትገሠግሣለች። በምድር የምትኖሩም ጽድቅ መሥራትን ተማሩ።
ኢሳይያስ 26:9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤ መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች። ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ።
ኢሳይያስ 26:9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።
ኢሳይያስ 26:9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።

