ኢሳይያስ 14:9-16

ኢሳይያስ 14:9-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ሲኦ​ልም በመ​ም​ጣ​ትህ ልት​ገ​ና​ኝህ በታች ታወ​ከች፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ከዙ​ፋ​ና​ቸው ያስ​ነሡ፥ ምድ​ርን የገ​ዙ​አት አር​በ​ኞች ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት በአ​ንተ ላይ ተነሡ። እነ​ዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ተይ​ዘ​ሃል፤ እንደ እኛም ተቈ​ጥ​ረ​ሃል። ከክ​ብ​ርህ ወደ ሲኦል ወደ​ቅህ፤ በበ​ታ​ች​ህም ብል ተነ​ጥ​ፎ​አል፤ ትልም መደ​ረ​ቢ​ያህ ሆኖ​አል” ብለው ይመ​ል​ሱ​ል​ሃል። “አንተ በን​ጋት የሚ​ወጣ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ሆይ፥ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወደ​ቅህ! ወደ አሕ​ዛ​ብም መል​እ​ክ​ትን የላ​ክህ አንተ ሆይ፥ እን​ዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀ​ጠ​ቀ​ጥህ! አን​ተም በል​ብህ፦ ወደ ሰማይ ዐር​ጋ​ለሁ፤ ዙፋ​ኔ​ንም ከሰ​ማይ ከዋ​ክ​ብት በላይ ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በሰ​ሜ​ንም ዳርቻ በረ​ዣ​ዥም ተራ​ሮች ላይ እቀ​መ​ጣ​ለሁ፤ ከደ​መ​ና​ዎች ከፍታ በላይ ዐር​ጋ​ለሁ፤ በል​ዑ​ልም እመ​ሰ​ላ​ለሁ አልህ። ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወ​ድ​ቃ​ለህ፤ ወደ ምድር ጥል​ቅም ትወ​ር​ዳ​ለህ። የሚ​መ​ለ​ከ​ቱ​ህም ይደ​ነ​ቃሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፦ በውኑ ምድ​ርን ያን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንም ያና​ወጠ፥

ኢሳይያስ 14:9-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በመጣህ ጊዜ ሲኦል ልትቀበልህ ተነሣሥታለች፤ ይቀበሉህም ዘንድ የሙታንን መናፍስት፣ በዓለም ገዥ የነበሩትን ሁሉ ቀስቅሳለች፤ በአሕዛብ ላይ የነገሡትን ነገሥታት ከዙፋናቸው አውርዳለች። እነርሱ ሁሉ ይመልሱልሃል፤ እንዲህም ይሉሃል፤ “አንተም እንደ እኛ ደከምህ፤ እንደ እኛም ሆንህ።” ክብርህ፣ ከነበገና ድምፁ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ብሎች ከበታችህ ተነጥፈዋል፤ ትሎችም መደረቢያህ ይሆናሉ። አንተ የንጋት ልጅ፣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፤ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አንተ ቀድሞ መንግሥታትን ያዋረድህ፣ እንዴት ወደ ምድር ተጣልህ! በልብህም እንዲህ አልህ፤ “ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፤ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ አደርጋለሁ፤ በተራራው መሰብሰቢያ፣ በተቀደሰውም ተራራ ከፍታ ላይ በዙፋኔ እቀመጣለሁ፤ ከደመናዎችም ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፤ ራሴንም እንደ ልዑል አደርጋለሁ።” ነገር ግን ወደ ሲኦል፣ ወደ ጥልቁም ጕድጓድ ወርደሃል። የሚያዩህም አትኵረው እየተመለከቱህ፣ በመገረም ስለ አንተ እንዲህ ይላሉ፤ “ያ ምድርን ያናወጠ፣ መንግሥታትን ያንቀጠቀጠ፣ ይህ ሰው ነውን?

ኢሳይያስ 14:9-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፥ የሞቱትንም፥ የምድርንም ታላላቆች ሁሉ፥ ለአንተ አንቀሳቀሰች፥ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች። እነዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃልን? እኛንስ መስለሃልን? ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፥ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፥ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል ብለው ይመልሱልሃል። አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴትስ ከምድር ድረስ ተቆረጥህ! አንተም በልብህ፦ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፥ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ። ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ። የሚያዩህ ይመለከቱሃልና፦ በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፥ መንግሥታትንም ያናወጠ፥

ኢሳይያስ 14:9-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“የሙታን ዓለም የባቢሎንን ንጉሥ ለመቀበል ተዘጋጅታለች፤ የሙታን መናፍስትም ሁሉ እርሱን ለመቀበል ይንቀሳቀሳሉ፤ በምድር ላይ ኀያላን የነበሩ እጅ ይነሡታል፤ ነገሥታት የነበሩትም ከዙፋናቸው ይነሡለታል። እንዲህም ይሉታል፥ ‘አንተም ደግሞ እንደኛ ደካማ ሆንክ! ከእኛም እንደ አንዱ ሆንክ ቀድሞ ስለ ክብርህ በመሰንቆ ይዘመርልህ የነበረው ቆመ፤ አሁን አንተ በትዕቢትህ ወደ ሙታን ዓለም ወረድክ። ስለዚህ አልጋህ ምስጥ፥ ልብስህም የትል መንጋ ሆኖአል።’ ” አንተ በሚያበራው የአጥቢያ ኮከብ የተመሰልክ የባቢሎን ንጉሥ ሆይ! እንደ ሰማይ ከፍ ካለው ክብርህ እንዴት ወደቅኽ! መንግሥታትን ሁሉ ታዋርድ ነበር፤ አሁን ግን ወደ መሬት ተጣልክ። አንተ እንዲህ ብለህ አስበህ ነበር፦ “ወደ ሰማይ ወጥቼ ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ዙፋኔን እዘረጋለሁ፤ በስተሰሜን ዳርቻ አማልክት በሚሰበሰቡበት ቦታ በተራራ ላይ እቀመጣለሁ። ከደመናዎችም በላይ ወጥቼ በልዑል አምላክ እመሰላለሁ” ብለህ አስበህ ነበር። ነገር ግን ወደ ሙታን ዓለም፥ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ወርደሃል። ሙታንም የአንተን ሁኔታ አይተው በመገረም ተመልክተው እንዲህ ይላሉ፦ “ያ ዓለምን ያንቀጠቀጠና መንግሥታትን ያናወጠ ሰው ይህ ነውን?

ኢሳይያስ 14:9-16 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፥ የምድርንም ታላላቆች ሁሉ፥ ለአንተ አንቀሳቀሰች፥ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች። እነዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃልን? እኛንስ መስለሃልን? ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፤ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፥ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል ብለው ይመልሱልሃል። አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴትስ ወደ ምድር ተጣልክ! አንተም በልብህ፦ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ። ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ። የሚያዩህ ይመለከቱሃልና፦ በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፥ መንግሥታትንም ያናወጠ፥