ኢሳይያስ 14:12
ኢሳይያስ 14:12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“አንተ በንጋት የሚወጣ የአጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብም መልእክትን የላክህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ!
ኢሳይያስ 14:12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አንተ የንጋት ልጅ፣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፤ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አንተ ቀድሞ መንግሥታትን ያዋረድህ፣ እንዴት ወደ ምድር ተጣልህ!
ኢሳይያስ 14:12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴትስ ከምድር ድረስ ተቆረጥህ!