ኢሳይያስ 11:10 - Compare All Versions

ኢሳይያስ 11:10 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በዚ​ያም ቀን የእ​ሴይ ሥር ይቆ​ማል፤ የተ​ሾ​መ​ውም የአ​ሕ​ዛብ አለቃ ይሆ​ናል፤ አሕ​ዛ​ብም በእ​ርሱ ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ ማረ​ፊ​ያ​ውም የተ​ከ​በረ ይሆ​ናል።

ኢሳይያስ 11:10 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚያም ቀን፣ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ አሕዛብ እርሱን ይፈልጋሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል።

ኢሳይያስ 11:10 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ለአሕዛብ ምልክት ሊሆን የቆመውን የእሴይን ሥር አሕዛብ ይፈልጉታል፥ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።

ኢሳይያስ 11:10 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በዚያን ጊዜ የእሴይ (የዳዊት) ዘር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ ሕዝቦች እርሱን ይፈልጉታል፤ መኖሪያውም የተከበረ ይሆናል።

ኢሳይያስ 11:10 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በዚያን ቀን፤ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ መንግሥታት ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል።