ኢሳይያስ 10:1 - Compare All Versions

ኢሳይያስ 10:1 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣ ጭቈና የሞላበትን ሥርዐት ለሚደነግጉ ወዮላቸው!

ኢሳይያስ 10:1-2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፥ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!

ኢሳይያስ 10:1 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሕዝቤን የሚጨቊን ግፍ የሞላበት ሕግ ለምታወጡ ወዮላችሁ!

ኢሳይያስ 10:1 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፤ ጭቈና የሞላበትን ሥርዓት ለሚደነግጉ ወዮላቸው!