ኢሳይያስ 1:18-20
ኢሳይያስ 1:18-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ። እሽ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኋለች፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
ያጋሩ
ኢሳይያስ 1 ያንብቡኢሳይያስ 1:18-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ኑና እንዋቀሥ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ፣ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም፣ እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል። ዕሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብላችሁ ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል።” የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሯልና።
ያጋሩ
ኢሳይያስ 1 ያንብቡኢሳይያስ 1:18-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፥ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፥ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፥ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
ያጋሩ
ኢሳይያስ 1 ያንብቡ